ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እርምጃው የማይቆም ከሆነ በፍጥነት ጨርሰው ወደ ሰላማችን መልሱን – ድምጻዊት ትርሀስ ታረቀኝ (ኮበሌ)
By: Date: November 13, 2020 Categories: የግል እይታ Tags:

ትንሽ መረጋጋት ተሰምቶኛል:: የእናቴንና የቤተሰቦቸን ሰላም መሆን ዛሬ ከትግራይ የወጡ ሰወች መልክት ኣድርሰውኛል:: የትግራይ መንግስት መሪወች ከመከላከያ ሠራዊቱና ከዋናው መንግስት ጋር ስምምነት አድርገው ወደ ሰላማችን ብንመለስ ይሻላል::

ትናንት በዙሪያየ ያሉ ሰወች የተከዘ ግድብ በኣብይ ትዛዝ በጀት ተደበደበ ሲሉ የነበረ ቢሆንም እኔ ደግሞ ተከዘ ግድብ በጀት ቢደበደብ አካባቢው በጎርፍ ተጥለቅልቆ የአለም ሚድያወች ይዘግቡት ነበር ብየ ስላቸው ነበር:: እንደ ሰማሁት ተከዘ ግድብ ምንም አልሆነም የከባድ መሳርያወች ያሉበት ቦታ ነው የተደበደበው።

የተቸገርኩት ነገር የማንን መረጃ ማመን እንዳለብኝ ነው። የማምናቸው ሰወች የሚነግሩኝ ነገር በሙሉ ወድያውኑ ውሸት መሆኑን ሳረጋግጥ ማንን ማመን እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል። ቀዳማይ ምንስተር ኣብይ በትግራይ ላይ እየወሰዱ ያሉትን እርምጃ መቆሙ ካልቀረ ቶሎ በፍጥነት ጨርሰው ወይም ተደራድረው ወደ ሰላማችን እንድንመለስ ምኞተ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *