“ወደ ህክምና ስንወስዳት የምትረሸን መስሏት ታለቅ ነበር

ገና የ17 ዓመት ታዳጊ የትግራይ ልዩ ኃይል ናት። ጀማሪ እንደሆነች የሚገልጽ የኮንስታብልነት መታወቂያ ይዛለች። ከአቅሟ በላይ የሆነ የልዩ ኃይል ሬንጀር እና ብቻውን ብትለብሰው እንደጉርድ የሚያገለግል ረጅም የመከላከያ ሰራዊቶች የሚለብሱት ቲሸርት አልብሰዋታል።

ወደ ሆስፒታላችን ስትመጣ ሁለቱንም እግሮቿንና ሁለቱን እጆቿን በጥይት ተመትታ ነበር። የጸጥታ ኃይሎች ለተሻለ ህክምና ብለው ወደ እኛ ሆስፒታል በመኪና ጭነው አምጥተዋታል። ምናልባት እየተነገራት ካደገችው ነገር የተነሳ በስልጠናም ወቅት ትሰማ ከነበረው አማራ ጨካኝ ነው ከሚል የውሸት ተረክ በመነሳት ይመስለኛል ሙሉ መንገዱን እያለቀሰች ነበር የመጣችው፣ዓይኖቿ እምባ ጨርሰዋል። ማልቀስ አቅቷታል፣ከመኪና አውርደን ስትሬቸር ላይ ስናስቀምጣት ወደ መረሸኛ ቦታ ልንወስዳት ስለመሰላት አመርራ ማልቀስ ጀመረች፤ልጅቱ አማርኛ ትንሽ ትንሽ ትሰማለች ግን መናገር አትችልም። ወደ ድንገተኛ ክፍላችን አስገብተን አስፈላጊውን ህክምና እያደረግን በጎን ትግርኛ የሚናገር የሚያጽናናት እና የምናደርግላትን የሚናገር ሰው መድበን ስራችንን ቀጠልን።

ልጅቱ ህጻን ልጅ ስናባብለው እንደሚመለሰው ትንሽ ቆይታ ስተረጋጋ፣በፍቅር እና በስስት ዓይን ስታየን እታዘባት ነበር።ምናልባት ይገድሉኝ ይሆን ብላ የፈራችው የውሸት ታሪክ እንደነበር የገባት ይመስለኛል። እየተረጋጋች በትክክል ምላሽ መስጠት ጀመረች።

አስፈላጊውን ህክምና አድርገን ስንጨርስ ወደ ጎንደር ለተጨማሪ ህክምና እንደምንልካት ሲነገራት ከእኛ መነጠል ጨነቃትና እንደገና አምርራ ማልቀስ ጀመረች። አሁንም ወደ መረሸኛ ቦታ የምትወሰድ ያክል በፍራት ትርበተበት ነበር። ህወሃት በምርከኞች ሲያደርግ የያየችውን፣አማራም ያደርጋል እየተባለ የተነገራትን ነገር ከውስጧ ማውጣት ያቃታት ይመስለኛል።ብቻ እያጽናናን ላክናት።በሆስፒታል ውስጥ የነበሩ ታካሚዎችና አስታማሚዎች እኔን እያሉ ደረታቸውን እየደቁ ሀዘኔታቸውን ይገልጹ ነበር።ወጣቶች ጠምቷት ይሆናል በሚል ጭማቂና ውሀ ፍለጋ ይሯሯጡ ነበር።

ይች ታዳጊ ምናልባት የአንድ ድሀ ቤተሰብ ልጅ ናት ህወሃት በውሸት የጀብደኝነት ወኔ እያጋጋለ ስለ አማራ ስለ ወንድሞቿ እንዳታውቅ የልጅነት አዕምሮዋን በጥላቻ በክሎት ኖሯል።ይች ልጅ እግዚአብሔር ጤናዋን መልሶ እና እድሜ ሰጥቷት ሀገር ሰላም ሲሆን ያሳለፈችውን ታሪክ ትናገራለች ብየ አስባለሁ።በእርግጠኝነት የአማራ ህዝብ ስላደረገላት እንክብካቤ ህወሃትን እየረገመች እንደምትመሰክር አልጠራጠርም።

እግዚአብሔርን ፈርተን በልባችን ያተመውን የሰብአዊነት ስፍር ሳናጓድል በልዕልና እንደምንኖር እንዲታወቅልን እንፈልጋለን። እጆቻችን በምርኮኞች፣በንጹሐን ሊነሱ አይችሉም ይህ እያንዳንዱ አማራ ሳይነጋገር አንድ ዓይነት ምላሽ የሚሰጥበት ጉዳይ ነው።ህወሃት ግፈኛ ነው በአካል ካደረሰው በደል በላይ በንጹሐን ህጻናት አዕምሮ አማራን በእኩይ ገባሪነት ለመሳል በመሞከር ማባሪያ የሌለው ጸረ አማራነት እንዲኖር እያደረገው የኖረው እና አሁንም እያደረገው ያለው ርኩስ ተግባር ያይላል።እያንዳንዱ ትግራዋይ የአማራን ሰብአዊ መልካም ግብር በአይኑ እንዲያይና እንዲመሰክር እያደረግን ነው። Via Getachew Shiferaw

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *