ሽራሮ የአኬልዳማ ምድር የወያኔ አውሬነት ማሳያ

ጀግናው የኢትይጵያ መከላከያ ሰራዊውት ሽራሮን ከስግብግቡ የህወሃት ጁንታ ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ ነጻ አውጥቶ ተቆጣጥሮታል። ይሁን እንጂ መከላከያው በድል አድራጊነት ሽራሮ ሲገባ የስግብግቡን ጁንታ የመጨረሻ የጭካኔ ባህሪ የሚያሳዩ ድርጊቶች አግኝቷል። ድል አድራጊው መከላከያ ሰራዊት በሽራሮ እጅና እግራቸው የፍጥኝ ታስሮ እርቃናቸውን የተረሸኑ የበርካታ የመከላከያ ሰራዊት አስከሬኖችን አግኝቷል።

በኢትዮጵያ ህዝብ ባህል እና ስነምግባር እንኳን ክቡሩ የሰው ልጅ እንስሳት እንኳን እንደታሰሩ አይታረዱም። ይህ ስግብግቡ የህወሃት ጁንታ ምን ያህል ከኢትዮጵየ ስነምግባር ያፈነገጠ አውሬያዊ ማንነት ያለው መሆኑን በገሃድ ያረጋገጠ እውነታ ነው።

ድል አድራጊው መከላከያ ሰራዊት በዚህ ዘግናኝ ድርጊት እጅግ በማዘኑና በመበሳጨቱ በደም ፍላት ቤት በማቃጠልና ሌሎች እርምጃዎችን በመውሰድ ጉዳት እንዳያደርስ የሃገር ሽማግ ሌዎች ወጥተው እግሩ ላይ ወድቀው ተማጽነው አረጋግተውታል። በዛሬው ዕለት እጅግ በሚዘገንን ጭካኔ የተገደሉት የመከላከያ ሰራዊት አባላት የቀብር ስርአት በክብር ተፈጽሟል።አሁን መከላከያ ሰራዊቱ ነጻ ያወጣውን የሽራሮ አካባቢ ተረጋግቶ እየተቆጣጣረ ነው።

ሰራዊቱ የድል ግስጋሴውን ቀጥሎ ሌሎች ከተሞችን ሲቆጣጣረ ከዚህ የከፋ ዘግናኝ የስግብግቡ ህወሃት ጁንታ ድርጊቶች ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ ይጠበቃል። በመከላከያ ሰራዊት ነጻ የሚወጡ አካባቢዎች የሚኖረው የትግራይ ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመግባበት ሊረረጋጋ ይገባል። (ስዩም ተሾመ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *