5ተኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር በትንሹ ምን ተፈጠረ

ደሜን ትጠጣለህ እንጂ እጄን አትጨብጣትም ብ/ጄኔራል ሙሉዓለም አድማሱ በከበባው ወቅት ለህወሃት ልዩ ሀይል በማክራፎን ያስተላለፈው መልክት ከሶስት ቀን ውጊያ በኃላ ሞገደኛው ብ/ጄ ጠላትን መክቶ አባበረ

ኩነት 1:- አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ አባላት ፈቃድ በመጠየቅ ፈቃድ ጠይቀው ነበር:: በዚህ ቆይታቸው ኦረንቴሽን ወስደው ነበር የተመለሱት::ከተመለሱም ቀን ጀምሮ የባህሪይ ለውጥ ይታይባቸው ነበር::ለምሳሌ ስልክ በምስጢር ማውራት በቡድን መቀመጥ በተለይ የሰኞ አለት ደብረ ፅዮን መግለጫ ተከትሎ ይህ መገለሉ በተደጋጋሚ ይታይ ነበር::

ኩነት 2:- ማክሰኞ ሌሊት 4 አካባቢ ጦሩ ከውስጥ ባሉት የትግራይ ተወላጆች ስምሪት ሰጭነት ባላወቀው መንገድ ጨለማን ተገን አድርጎ ተከቦ ነበር::

ኩነት 3:- ሲቪል የለበሱ የትግራይ የልዩ ሃይል አባላት ዋርድያዎችን ጀነራል ሙሉ አለምን ማግኘት እንደሚፈልጉ መጥተው አናገሯቸው::አላማው ጄኔራሉን ኢላማ ውስጥ በማስገባት መምታት ነበር:: ዋርድያዎቹ መግባት እንደማይችሉ ቢነግሯቸውም ሰብረው ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ ርምጃ ወስዱባቸው::ከዚያች ሰአት ጀምሮ በውስጥ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ አባላት በውጭ የሚገኙት የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት እርምጃ መውሰድ ጀመሩ::ስለነበር ሁሉም የመከላከያ አባላት በድንጋጤ ተነሱ ያኔ መብራት ስልክ አቋርጠውባቸው ስለነበር እና ዱብ እዳ በመሆኑ ነገሮች ከባድ ነበር::

ኩነት 4:- ወታደሮቹ ጀነራሉን እንዲሸሽ ቢለምኑትም የትም እንደማይሄድ እስከመጨረሻው ድረስ ከልጆቹ ጋር እንደሚሰዋ ካምፑ ውስጥ በሚገኘው የድምፅ ማጉያ ይነራቸው ነበር:: የተኩስ ልውውጡ በውስጥም በውጭም ከባድ ሁኔታ ቀጠለ::ይህ ጦር ጭንቅ ውስጥ በነበረበት ሰአት አድፍጦ ጥቃት ሲሰነር የነበረው ልዩ ሃይል ሲበተን እና ጋብ ሲል ሲመልከቱ ግራ ገብቷቸው ነበር::ወዲያው አይዟችሁ አይዟችሁ ደርሰናል የሚል ድምፅ ይሰሙ ነበር:: የአማራ ልዩ ሃይል እና ፋኖ ነበር:: የተሸከሙትን ባንዴራ መሬት ላይ ተከሉት ያኔ ጀነራል ሙሉአለም እና ወታደሮቹ በደስታ ተዋጡ:: ከዚያማ ምን አለው የአማራው ተራራው እሳት በላይ እና በታች እንደሶዶም እና ጎሞራ ከከሃዲዎቹ ላይ ዘነበባቸው!!

5ተኛ ሜካናይዝድ ክፍል ጦር ነፃ ወጣ!! (ናትናኤል መኮንን እንዳሰራጨው)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *