አስመሳዮች ልሳናችሁንና እጃችሁን ሰብስቡ

ሰላማዊ መፍትሄ፣ ድርድር፣ በጦርነት አሸናፊም ተሸናፊም የለም፣ ጦርነት አውዳሚ ነው፣ በወንድማማቾች መካከል የሚደረግ ጦርነት ወዘተ እያላችሁ በሕዝብ ቁስል ላይ እንጨት አትስደዱ። ስልታዊና ብልጣ ብልጥ ድጋፋችሁን ሰው የማይነቃባችሁ እየመሰላችሁ አትሸወዱ።

የኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ጦርነት ውስጥ አልገባም፤ በወንድማማቾች መካከልም የሚደረግ ጦርነት የለም። መከላከያ ሠራዊታችን የትግራይን ሕዝብ ነጻነት አሳጥቶ አካባቢውን የጦርነት አውድማ አደርጋለሁ በሚለው የትህነግ/ህወኃት ጉጀሌ ላይ ህግ የማስከበርና ሥርዓት የማስፈን እርምጃ እየወሰደ ነው። በአስከፊ የጭቆና ቀንበር ውስጥ የሚገኘው የትግራይ ሕዝብ ከጭቆና ወጥቶ ወንጀለኞችን ከተደበቁበት ጉሬ ፈልጎ በማደን ለህግ አስከባሪ አካላት ያስረክባል።

የትግራይ ሕዝብ ከራሱ አብራክ በወጡ ሌባ፣ ደም መጣጭ አረመኔ የጥቂቶች ቡድን ምክንያት የሚደርስበት የስነልቦና ጫና ቀላል የሚባል አይደለም። ነገ ከዛሬ ይሻላል በማለት በተሰፋ ስሜት ለ30 ዓመታት ህወሓት በሕዝቡ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ደም አፍሳሽ የአንድ መንደርና የአንድ ቤተሰብ በዝባዥና ገዳይ ሥርዓት መመስረቱን ሁሉም ትግራውይ ተረድቶታል።

የመከላከያ ሠራዊታችን የሚወስደው ህግ የማስከበርና ሰላምን የማስፈን እርምጃ በድንበር አካባቢ የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች እየደገፉት ይገኛሉ። በዚህ መካከል የህግ ማስከበር ሂደቱን ለማጨናገፍ ድርድር እና ጦርነቱ ይቁም የሚሉ አስመሳዮች ከድርጊታቸው መቆጠብ ይገባቸዋል። ብሩክ አበጋዝ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *