ህወሓትን ማዳከም ወይም ማስወገድ ( ዶክተር ታደሰ ብሩ)

በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሜ እጽፋለሁ። ህወሓት ገና አልተሸነፈም፤ ተፈጥሮዉን ቀይሮ ሽብርተኛ ከፊል መንግስት (Terrorist Semi State) ሆኗል። እንዲህ ዓይነት ሽብርተኛ ድርጅት የምናውቀው ISIS ነው። ህወሓት ሳይሸነፍ አገር ማረጋጋት ፈጽሞ አይቻልም።

ህወሓት እንዴት ማዳከም እንደሚቻል ስልት ለመንደፍ ISIS እንዴት እንደተዳከመ ማጥናት ይጠቅማል። ፀረ-ህወሓት broad coalition መፍጠር በጣም አስፈላጊ ነው። ሁለገብ የትግል ስልቶችን መጠቀም ተመራጭ ነው። ህወሓትን ከውስጥም ከውጭም ማዳከም ይገባል፤ ማዳከም ካልተሳካ በትግራይ ክልል ከያዘው የመንግስት ስልጣን ማስወገድ ይገባል።

ህወሓት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው አገሮች ሁሉ ስጋት እንደሆነ የአካባቢው አገሮች መንግስታትን ማሳመን ተገቢ ነው። እየተደረገ ያለው ግን ወደዚያ የሚያመራ ስለመሆኑ በበኩሌ እርግጠኛ አይደለሁም። እንዲያውም ከራሱ የጎለበተ ሠራዊት በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ ያለውን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ሊያማልልና ሊጠቀም ይችላል።

ከወታደራዊ አቅሙ በተጨማሪ የፋይናንስ፣ የዲፕሎማሲና የፕሮፖጋንዳ አቅሙም ጎልብቷል። በድርድር የሚያራዝመው እድሜው ለተጨማሪ ጥፋቶች ራሱን ይበልጥ የሚያደራጅበት ይሆናል። ህወሓት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በቀጠናው የደቀነው አደጋ የማያባራ እልቂት ሊፈጥር የሚችል ነው።

በዚህ የመጨረሻ ሰዓትም ቢሆንም የዶ/ር አቢይ መንግስት ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ ነጥሎ የሚያዳክምበት ካልሆነም የሚያስወግድበት ስልቶችን ነድፎ ተግባራዊ ካላደረገ በራሱና በአገራችን ከዚያም አልፎ በአፍሪቃ ቀንድ የማያባራ እልቂት እየጠራ እንደሆነ ይገንዘብ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *