የትራምፕ ግዴለሽ የሆነና ጥንቃቄ የጎደለው ንግግር በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት ሊፈጥር ይችላል ተባለ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አስተያየት ለግብጽ ወገንተኝነት የታየበት፣ ስለግደቡ ትክክለኛ መረጃ እንደሌላቸው እና ኢትዮጵያዊያንን በአግባቡ እንደማያውቁ የተያበት ነው ሱሉ የታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ።

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን የትናንት ምሽት ንግግር ተከትሎ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ የሰጡት ዶ/ር አረጋዊ በርሔ እንደተናገሩት፤ የፕሬዝዳንቱ አስተያየት አሜሪካ ለግብጽ ያላትን ወገንተኝነት ዳግም በግልጽ ያሳየ ነው ብለዋል።

የፕሬዝዳንቱ ንግግር ከአንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሚጠበቅ አይደለም ያሉት ዶ/ር አረጋዊ፤ ንግግራቸው ለግብጽ ያላቸውን ወገንተኝነት በግልጽ ያሳየ ነው። ይሄ ደግሞ የሆነው አገራቸው ከእስራኤል እና ከግብጽ ጋር ካላት ግንኙነት ጋር ይያያዛል ሲሉም ነው ያብራሩት።

“ግድቡ የተጀመረውና እዚህ የደረሰው በህዝብ ድጋፍ ነው፤ ዳር የሚደርሰውም በህዝብ ድጋፍ ነው፤ አሁንም ከተባበርን ይሄን አይደለም ሌላ ግድብ መስራት እንችላለን” ያሉት ዶ/ር አረጋዊ፤ ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ለግድቡ ያለውን ድጋፍና ተሳትፎ በአግባቡ እንዳልተረዱት ንግግራቸው ያሳያል ብለዋል።

ኢትዮጵያን የወረረው ጣሊያን አድዋ ላይ ድል የተነሳው በኢትዮጵያዊያን ትብብር እንጂ በውጭ ሀይል ድጋፍ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ አሁንም ከ70 በመቶ በላይ የደረሰን ግድብ ለማጠናቀቅ የሚያቆመን ምንም አይነት ሀይል የለም ሲሉ ነው የመንግስትንና የህዝቡን የትብብር መንፈስ ያስረዱት።

አንድ አንዱ ንግግራቸው ኢትዮጵያን በውል ካለማወቅ የመነጨና ኢትዮጵያዊያንም አገራቸውንና ድንበራቸወን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ካለመገንዘብ የተነሳ የሰጡት ሃሳብ ስለሆነ እንደ እርሳቸው አይነት ካላ ፕሬዝዳንት የሚጠቅ ንግግር ነው ሲሉም ነው ዶ/ር አረጋዊ የተናገሩት።

ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ የጀመረችው ለጋራ ተጠቀሚነት መሆኑ እየታወቀ የዚህ አይነት ማስፈራሪያ መሰንዘር ፋይዳ የሌለው መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር አረጋዊ፤ ኢትዮጵያዊያን በዛቻና ማስፈራሪያ የማይንበረከኩ መሆናቸውን ማወቅ ያስፈልጋል ሲሉም ነው የፕሬዝዳንቱን ንግግር የተቹት።

“በውስጥም በውጭም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ተበብረን ግድቡን ከዳር ለማድረስ መፍትሄው በእጃችን ነውና አሁን ካለውም በላይ መተባበር አለብን” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል። ኢፕድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *