የህንፃ ስር ፓርኪንግ ቦታዎችን ለሌላ አገልግሎት ያዋሉ ህንፃዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የፓርኪንግ እና ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2013 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የህንፃ ስር ፓርኪግ ስፍራ አጠቃቀምን በተመለከተ 200 ህንፃዎች ላይ ፍተሻ አደረገ፡፡

ኤጀንሲው ከከተማዋ ግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን ጋር በመሆን ከመገናኛ ጎላጉል ቦሌ መድኃኒአለም፣ ከጎላጉል ኡራኤል ቦሌ መድሃኒአለም፣ ከኡራኤል እስጢፋኖስ አከባቢ በሚገኙ 200 ህንፃዎች ላይ ለፓርኪንግ የተዘጋጁ የህንፃ ስር ፓርኪንግ ቦታ አጠቃቀም ላይ ፍተሻ አድርጎ 30ዎቹ ከታለመለት ዓላማ ውጭ ሙሉ በሙሉ በመቀየር ለሌላ አገልግሎት ያዋሉ ሲሆን፣ 30ዎቹ በከፊል ለሌላ አገልግሎት ማዋላቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የፓርንግ ቦታዎቹን ለሌላ ዓላማ ያዋሉ የህንፃ ባለቤቶች የቃል እና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን በቀጣይም የፓርኪንግ ቦታዎቹን ለታለመላቸው ዓላማ ተግባራዊ የማያደርጉ የህንፃ ባለቤቶች ላይ በንግድ ቢሮ በኩል ንግድ ፈቃዳቸው እንዲነጠቅ እና ህንፃዎቹ አገልግሎት እንዳይሰጡ እስከማሸግ እርምጃ እንዲወሰድ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል፡፡

በተጨማሪም ዳይሬክቶሬቱ የመንገድ ላይ ፓርኪንግ አጠቃቀምንም ወደ ስርዓት የማስገባት ስራ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፣ በዘርፉ የተሰማሩት 96 ማህበረት በኤጀንሲው ደረሰኝ የፓርኪንግ አገልግሎትን እንዲሰጡ ለማድረግ ከጥቃቅን እና አነስተኛ ጋር እያስተዳደረ ይገኛል፡፡ ለማህበራቱ በደረሰኝ አጠቃቀም እና በሌሎች የአስተዳደር ስራዎች ያሉባቸውን ክፍተቶች ለመሙላት ለ25 ማህበራትም ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ኤጀንሲው በቀጣይም የህንፃ ስር ፓርኪንግ አጠቃቀምን ወደ ስርዓት በማስገባት ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ እና የመንገድ ላይ ፓርኪንግ አገልግሎት አሰጣጥ በማህበራት ደራጅተው አገልግሎት የሚሰጡት በኤጀንሲው ደረሰኝ እንዲጠቀሙ የማድረጉ ሂደት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ TMA የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//dooloust.net/4/4057774