በባለስልጣናቱ የትምህርት ማስረጃ ዙርያ አበበ ገላው ለአቻምዬለህ ታምሩ የሰጠው ምላሽ

አቻምየለህ ታምሩ ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ የትምህርት ማስረጃ ባቀረብኩት ሪፖርት ላይ የሰጠውን አስተያየት በመገረም አነበብኩት። የገረመኝም ትናንት በሜሰንጀር ተመሳሳይ አስተያየት ልኮልኝ አስተያየቱ ስህተት ስለነበረው እርምት አድርጌበት ነበር። ይኸውም ከዚህ በፊት ስለ አባዱላ ሃሰተኛ ዲግሪዎች በጻፍከው ላይ ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ የተጭበረበረ ዲግሪ ወስዷል ብለህ ነበር። አሁን ግን የራስህን ሪፖርት ተጻረርከው የሚል ይዘት የነበረው ነው። እኔም በምላሼ ትክክል አይደለም። ይታረም የሚል ምላሽ ሰጥቼ ነበር።

የእኔ ዘገባ ያተኮረው አባዱላ አገኘሁ ባላቸው የባችለርና የማስተርስ ዲግሪዎች ሲሆን እነዚህም ዲግሪዎች የተገዙት ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ [Century University] እንጂ ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ግሪንውች [University of Greenwich] አይደለም ብዬ መልሼለት ነበር።

ስህተቱን ደግሞ እያወቁ እንደ መረጃ ማቅረብ ፈጽሞ ትክክል አይደለም። አቻምየለህ ያልጻፍኩትን አንብቦ አልክ ብሎ የጠቀሰውን ጥቅስ ከየት እንዳመጣው ቢያሳየኝ ትልቅ ውለታ እንደዋለለኝ እቆጥረዋለሁ። ያልተጻፈ ማንበብ ትክክል አይደለም።

ሌላው ሽፈራው ሽጎጤ ያነበበውን እንደ መረጃ ማቅረብ ብዙም አያስኬድም። ስህተተ ስለሆነ እርምት ይደረግበት ብሎ መጠየቅ ግን ተገቢ ይመስለኛል። እኔ ያቀረብኩት ሪፖርት መሰረት ሊረጋገጡ ይሚችሉ ሃቆችን መሰረት ያደረገ ነው። ዶክመቶች ጭምር እጄ አሉ።

ሌላው ጊዜ ወስጄ የልመረመርኩት ጉዳይ ላይ ሁሉ አስተያየት መስጠት አልችልም።ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ግሪንዊች ከ140 መታት በላይ ያስቆጠረ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲ ስለሆነ ለቀረበረው መላምታዊ ክስ ምልሽ እንዳይሰጥ ጥንቃቄ ይደረግ። ምላሹ ህጋዊ ይዘት እንዳይኖረው በመስጋት ነው ይሄን ይምለው። ለማንኛውም እኔ የዛሬ አምስት አመት የጻፍኩት ጽሁፍ ቃላቶቹ አልተቀየሩም። (አበበ ገላው ከአምስት አመት በፊት በኢካዴፍ ያቀረበው ጽሁፍ ይህን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *