ከአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ 8 ተሽከርካሪዎችን ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በኮሚሽኑ የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኢንስፔክተር ያሬድ አለማየሁ እንደገለፁት ከአዲስ አበባ ከተማ ተሰርቀው የተወሰዱ 8 የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ከአዲስ አበባ ውጪ በሚገኙ የተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ ይገኛል ብለዋል።

የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ቸልተኝነት እና ጥንቃቄ ጉድለት በተለይም ቁልፍ ሳይነቅሉ እና የተሟላ ጥበቃ ባለበት ስፍራ ሳያቆሙ መሄድ፣ በከተማችን የተሽከርካሪ ስርቆት ከሚፈፀምባቸው ምቹ ሁኔታዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ጉዳዮች በጉምሩክ ተይዘው የነበሩ እና ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 4 ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር እና ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ በፖሊስ በተደረገ ክትትል ተሽከርካሪዎቹ ወንጀሉን ፈፅመዋል ከተባሉት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//usounoul.com/4/4057774