አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባ አንድ ላይ እንዲገናኙ ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ አፈፃፀሙን ለመመልከት በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባ አንድ ላይ እንዲገናኙ ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ አፈፃፀሙን ለመመልከት በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተወካይም ቀርበው ትእዛዙ መፈፀሙን አብራርቷል።

እነ አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባም ትእዛዙ መፈፀሙን ገልፀዋል። የአቶ ሀምዛ አዳነ (ቦረና) እና የሸምሰዲን ጠሃ ጠበቃ ለችሎቱ ደንበኞቹ 30 ደቂቃ ብቻ አየር እያገኙ መሆኑን በመግለፅ፤ ከ30 ደቂቃ በላይ የፀሃይ ብርሃን እና አየር እንዲያገኙ ተእዛዝ እንዲሰጥለት ጠይቋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም በቂ አየር እና የፀሃይ ብርሃን እንዲያገኙ ትእዛዝ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በሰብአዊ መበት ጥሰት ወንጀል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት በእነ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ ከ15 በላይ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበው የአቃቤ ህግ ምስክር እየተሰማ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//naucaish.net/4/4057774