እንዶድ፣ የቢልሃርዝያ በሽታና አክሊሉ ለማ
By: Date: August 7, 2020 Categories: ጤና Tags:

እንዶድ አብዛኛውን ጊዜ በወንዝ ዳርቻዎች ይበቅላል። በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ልክ እንደሳሙና በሰፊው ለልብስ ማጠቢያነት ሲያገለግል የነበረ ሲሆን ከተክሉ የሚገኘው ጭማቂ ወይም ፍሬው ለቢልኻርዝያ በሽታ የሚዳርገውን ተህዋስ የሚያስጠልለውን ቀንድ አውጣ ስለሚገድል ለመድኃኒትነት ሊያገለግል እንደሚችል በመጠርጠር ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ ፕ/ር አክሊሉ ለማ ሲመራመሩበት ቆዩ። የሁዋላ የሁዋላም ምርምራቸው ፍሬ አግኝቶ ለቢልሃርዝያ በሽታ መድኃኒት ሊሰሩበት ቻሉ።

ከተክሉ የሚገኝ ጭማቂ አልቅትንም ስለሚገድል በውኃ ውስጥ የአልቅቶችን ቁጥር ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ተክሉ ለከብቶችመም የማይስማማ በመሆኑ እንስሳት ለምግብነት አይመርጡትም፡፡

ፕ/ር አክሊሉ ለማ በ1928 ዓ.ም. በጅጅጋ ከተማ ተወለዱ። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካገኙ በኋላ በአሜሪካ አገር ከሚገኘው ጆን ሆብኪንስ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።

አክሊሉ ለስራ ጉብኝት ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በሚዘዋወሩ ጊዜ ሰዎች በዕንዶድ የሚያጥቡበት አካባቢ ብዙ ቀንዳውጣዎች ሞተው በማየታቸው እንደመነሻ ሃሳብ በመውሰድ ከዶ/ር ለገሠ ወልደዮሐንስ ጋር በመተባበር ብልሃርዚያ ለተባለው በሽታ አምጪ ለሆነው የቀንድ ዓውጣ ለሰላሳ ዓመታት ተመራምረው “እንዶድ 44” የተባለ ቢልሀርዝያን ማጥፊያ መድሀኒት አግኝተዋል። ለዚህም ውጤታቸው “Right Livelihood Award” ሽልማት እና የአሜሪካ የፈጠራ ውጤት ባለቤትነት መረጋገጫ አግኝተዋል። ይቺ አገር፣ እንደ ቅጣው እጅጉ፣ ገቢሳ እጀታና አክሊሉ ለማ አይነት ድንቅ ሰዎች። (ሳይ-ቴክ እንዳቀረበው) ያስፈልጋታል የምትሉ ሼር አድርጉት!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *