ተጨማሪ ኮሮናን ለመከላከልና ለመዳን የሚጠቅሙ ጥቆማዎች
By: Date: August 7, 2020 Categories: ጤና Tags:

ከዶር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ – ትናንት በአንዳፍታ ሚዲያ ላይ ያስተላለፍኩት መልዕክት ያልደረሳችሁ ወገኖቼ የካናዳው የስነ-ምግብ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አባዛር ባስተላለፉት መረጃ መሰረት የኮሮና ቫይረስን እንዲዋጋና በሽታው ሳይከፋብን ቶሎ እንድንድን ነጭ የደም ሴሎቻችንን የሚያግዙልን ዋና ዋና ነገሮችን ላጋራችሁ።

1ኛ በቂ እረፍት ማግኘት (የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች የታዩበትም ሆነ ሊይዘኝ ይችላል ብሎ ያሰበ ሰው ከውጥረትና ከድካም ራሱን አግሎ ለብቻው እረፍት ማድረግ አለበት። ይህም የራሳቸው ክፍል ያላቸው ሰዎች ክፍላቸውን ዘግተው፤ አልያም የሌላቸው ሰዎች ከቤተሰብ ራቅ ብለው በቂ እረፍት ማድረግ አለባቸው። ነገር ግን ምልክቶቹ እየባሱ ከመጡ ማስክ አድርጎ በግል መኪና አልያም በኮንትራት ተሳፍሮ ወደ ጤና ማዕከል መሄድ ያስፈልጋል)

2ኛው የሰውነታችን የመከላከልን አቅምን ያግዛል የተባለው ሙቀት ማግኘትና ትኩስ ነገሮችን አብዝቶ መጠጣት ነው። በአገራችን እንደሚደረገው የማቃጠል ባህሪ ያላቸውን እንደ ነጭ ሽንኩርት ያሉ ተክሎችን አፍልቶ መጠቀም ጥቅም እንዳለው አምናለሁ።

3ኛው የቫይታሚን እንክብሎችን መውሰድ ሲሆን (በተለይ ቫይታሚን ዲ፣ ሲ እና ኤን ጨምሮ ሌሎቹንም የያዙ መልቲ ቪታሚን ኪኒኖችን ቀድሞ መውሰድ ሰውነታችን ለሚጠብቀው ፍልሚያ ዝግጅቱን ያጠናክርለታል፤ (ቫይታሚን መግዛት የማትችሉ የማህብረሰብ አካላት ደግሞ ፍራፍሬዎችን (ብርቱካንና ሎሚ) እያፈሉ ስኳር ሳያበዙ መጠጣትና አትክልቶችን በመጠኑ እያበሰሉ መመገብ ይችላሉ፤

4ኛ ላይ የምጠቁማችሁ ደግሞ የዚንክ እንክብሎችን ሲሆን የፋርማሲ ባለሙያው በሚያሳያችሁ መሰረት (ከ5-10 mg) በቀን መዋጥ ተመክሯል።
ይህ በሽታ በጣም ከፍተኛ የመግደል አቅም የሌለው ስለሆነ ራስን ከመጠበቅ ጎን ለጎን የሰውነት የመከላከያ አቅምን ማጠናከር ቶሎ ለመዳን ያግዛል። በተለይ አረጋውያን፣ የአስም፣ የስኳር፣ የኤች አይ ቪ፣ የልብና ኩላሊት ታማሚዎች ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።

በስተመጨረሻም ፍርሃት በራሱ የሰውነት የመከላከል አቅምን እንደሚቀንስ ጥናቶች ስለጠቆሙ ፍርሃትና ጭንቀታችንን ትተን በእውቀትና በእርጋታ ችግሩን እንድንወጣው አሳስባለሁኝ። (መልእክቱን ሼር በማድረግ ላልሰሙ አሰሙ ስል በአጽንኦት እጠይቃችኋለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ከክፉ ይጠብቅ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *