Press "Enter" to skip to content

ቢገድል ስለ ኢትዮጵያ – ቢገደል ለኢትዮጵያ! ~ ክብር ለአማራ ይሁን! (የትነበርክ ታደለ)

እንኳን ደስ ያላችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን! እስከዛሬ በታሪክና በአፈ ታሪክ ብቻ የምታውቁት ጠላት ገድሎ ሀገር የሰራው አማራ ዘንድሮ በወንድሞቹ እየሞተ ሀገርን አስቀጠለ! በሞቱ ኢትዮጵያን ከመፍረስ ታደገ! ክብር ለአማራ ይሁን!

ኢትዮጵያን የሰራት የሀገር ፍቅርን የዘራባት አማራ ጥንት ጠላት ገድሎ አኖራት ዘንድሮ ሀገር ሰርቶ የሰጣቸው ወንድሞቹ እየገደሉት አስከሬኑን ጎዳና ላይ እየጎተቱት፣ ቤት ንብረቱን በእሳት አንድደው ሲፎክሩ — ዛሬም ደግሞ ሀገር እንዳትፈርስ እያለ ሞቱን እያየው ኢትዮጵያን አኖራት!

ሞቱን እንኳ “እውነት እውነት አልመስል አለኝ” እያለ ሞቱን ማመን እያቃተው “ውሸት ነው” እያለ፣ ማን በሀገሩ እንደመጣበት እያወቀ፣ የሱ ሞት አላማው እየገባው፣ ቢገድል ሀገር እንዲያፈርስ ገብቶት፣ ሞቱ ሀገር እንደሚያኖር አምኖ በደስታ ሞተላት!

በስምንተኛው ሺህ ሲመሽ ተወልጄ፣
ጅቡን ጋሼ እላለሁ ተኩላውን ወዳጄ…
እያለ ስለ ሀገር – ስለ ኢትዮጵያ – አባቶቹ ሞተው ስላቆይዋት ሀገር ሲል ጅቡን እና ተኩላውን እየለመነ ሞተላት – ገድሎ እንዳያጠፋት!

አማራ ተሰርቶ ያለቀ ህዝብ!

አባቶቹ ክሽን ክትት አድርገው ሰርተው የጨረሱት ህዝብ፣ የሀገር ሀላፊነትን ለልጅ ልጆቹ እንደ ሀብት ርስት እየመረቀ እየሰጠ ሲገድሉት ተቀበሏት እያለ ወደ መቃብሩ በፈገግታ የሚሞት የስርዓት ህዝብ አማራ!

የፍቅር ህዝብ አማራ!
ዛሬ በገዛ ወንድሞቹ ከጀርባው እየታረደ ሀገር ትኑር እያለ በሰልፍ ወደ ሞት ይሄዳል!
ዜጋ ማን ነው? ኢትዮጵያዊ ማን ነው? የሀገርን ውስጠ ሚስጥር የተረዳ ህዝብ ማን ነው? ~ አማራ!!!

አማራ የሀገር ዋልታ መከታ!
አማራን ገደሉት!
ሞትክን ለኔ ያድርገው!
ሞትሽን ለኔ ያድርገው!
የኔን ሞት ሞትሽልኝ!
የነገዋን የልጄን ሀገር ጥለሽልኝ ለማለፍ ስትይ ሞትሽ!!

እንጂ መግደል ምን ያቅታል? መግደል ምን ይከብዳል? ቫይረስና ባክቴሪያ በሚሊየን ሊጨርሱን የተመዘገብን ዜጎች ደግሞ በዱላ ለመግደል ምን ይከብዳል? በቆንጨራና በሜንጫ አንገት መቀንጠስ ምን ይከብዳል? በደቦ ሰው መግደል ምን ይከብዳል?

የሚከብደውስ የመግደያው ምክኒያት ነው? አማራዬ ወገኖቼ ያላቸውን ለመግደል እንኳ ምክኒያት እያጣ ተገደለ፣ ለምን ልግደል ብሎ ሰበብ አጥቶ ተጨፈጨፈ! ሀገር ላኑር ብሎ ሞተ! ሀገር በኔ መግደል አይፍረስ ብሎ ወደ መቃብሩ ሄደ!

ሞትህን ለኔ ያድርገው!
ጀግኖቼ!
የቅድስት ኢትዮጵያ ሰማዕታት!
ሁሉን ለኔ ሳይል ቋንቋውን አጋርቶ፣ ባህሉን አጋርቶ፣ ህልሙን አጋርቶ፣ የሀይማኖቱን ሚስጥር አሳይቶ፣ ማንነቱ ጽፎ አስጠንቶ፣ በጨዋ ደንብ ህዝብ ሆኖ ዜጋ ሆኖ ሀገር ሰርቶ ሀገር እንዴት እንደምትሰራ አሳይቶ፣ ጥበብ አውርሶ – በገዛ ራሱ ዜጎች እጅ በብረት ተደብድቦ ሞተ!
ያንተ ሞት የኔም ነው! እኔንም ነው የገደሉኝ! አብረው ነው መንገድ ላይ የጎተቱን!!…

ተሰርተው ያላለቁ!
ያልተሰሩ!
በጫካ ህግ የሚኖሩ!
የሀይማኖት ህግ የማይገዛቸው!
ዜግነት ያልተገባቸው!
በሰውነትህ ልክ መቆም የማይችሉ ገና ሰው እንኳ ያልሆኑ!
አንተን በመግደል ሀገርን ማፍረስ ይቻላል ብለው ያመኑ ድኩማን!
አወክባቸውና ሞተህ ሀገሬን አኖርክልኝና ይበልጥ ጭራቅነታቸውን አለም እንዲያየው አደረክ!

አማራ!
ተሰርቶ አልቆ ሀገር መስራት የሚያስተምር ህዝብ! ~ አማራ!
አትሞትም!..… አማራነት አይገደልም! ኢትዮጵያ ገና ገና ገና ትኖራለች! ህልምህም ይሳካል! በሞትህ ህያው ያደረካት ኢትዮጵያ ታወድስሀለች! ታነግስሀለች! .…አማራዬ፣ የዜግነቴ ምንጭ! – አማራ ነኝ!!
አንተም አማራ ነኝ በል!

እንዲህ ያለው ክፉ ቀን ክፉ ሰው ላይ ጥሎኝ
እንኳን ልጅ ልንወልድ እኛንም አፋቶን
በለው! – ከሀገር ሊለይህ! ገድለህ ሀገር እንድታፈርስ ሲገድልህ! –
ክፉ ቀን! – ክፉ ሰው – ላይ ጥሎህ! –
ሞትህ ሀገር አስቀጠለ! ሞትህ ኢትዮጵያን አሻገረ!
ሞትህ እኔንም አነቃኝ!
አንተ ከሌለህ ኢትዮጵያ የለችም! አንተ ከሌለህ እኔም የለሁም!
አማራ ሆይ ብተውህ ቀኜ ትክዳኝ!!!

Be First to Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *