የነገው ግርዶሽ የትና ስንት ሰዓት ?

ነገ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60-80 ፐርሰነት ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡ ከ80 ፐርሰነት በላይ ያለውን ዋናውን ግርዶሽ ግን ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኝ ስፍራ ጎልቶ ይታያል፡፡

ግርዶሹ መታየት ከሚጀምርበት ምእራብ ኢትዮጵያ (ከጠዋቱ 12:50 ሰዓት) ጀምሮ ግርዶሹ እስከሚጠናቀቅበት ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ከጥዋቱ 3:25 ሰዓት) በአጠቃላይ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ይፈጅበታል።

ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች/ቦታዎች ቤጊ ፣ ሜቲ፣ መንዲ ፣ ጫልቱ ፣ ቡሬ ፣ አገው ግምጃቤት ፣ እንጅባራ ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ ፣ ዳሞት ፣ ጋይንት ፣ ንፋስ መውጫ ፣ ጋሸና ፣ ሙጃ ፣ ዋጃ ፣ ቆቦ ፣ ኮረም፣ አላማጣ ፣ ጊራራ እና ላልይበላ ይገኙበታል፡፡

በአዲስ አበባ ፤ ሐዋሳ ፤ ድሬደዋ ፤ መቐለ ፤ ደሴ ፤ አዳማ ፤ ባህር ዳር በመሳሰሉት ከተሞች ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን ይኖራቸዋል።

ከላይ ባለው ምስል ግርዶሹ የሚጀምርበትን ሰዓት ፣ ቀለበት ካለ ቀለበት የሚታይበትን ሰዓት ፣ ግርዶሹ የሚያልቅበት ሰዓት እንዲሁም ጸሃይ የምትሸፈንበትን መጠን መመልከት ትችላላችሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *