ኮሮናቫይረስን ከሌሊት ወፍ ተቀብሎ ወደ ሰው ያስተላለፈው የዱር እንስሳ የቱ ነው
By: Date: May 4, 2020 Categories: ትንታኔ Tags:

ኮሮናቫይረስን ከሌሊት ወፍ ተቀብሎ ወደ ሰው ያስተላለፈው የዱር እንስሳ የቱ ነው በቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተቀሰቀሰውና ወደ ተለያዩ የዓለም አገራት በመዛመት ላይ ያለው ኮረና ቫይረስ እንዴት ከእንስሳት ወደ ሰዎች እንደተላለፈ ለማወቅ ተመራማሪዎች ከባድ ጥናት ላይ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት ያለው መላምት በቻይና ጫካ ውስጥ ከተገኘ የሌሊት ወፍ እንጥብጣቢ ፈሳሽ በራሪ ነፍሳትን ወደሚመገቡ እንስሳት ተላልፎ በመጨረሻ ወደ ዱር እንስሳት ተዛምቷል የሚል ነው።

ከዚያም በቫይረሱ የተያዘ እንስሳ ሰው እጅ ወደቀ። ቫይረሱ ከዚህ ሰው የዱር እንስሳት መሸጫ ገበያ ውስጥ ወደሚሰሩ ሰዎች ሰዎች ተላልፎ በመጨረሻ የዛሬው ዓለም አቀፍ የኮሮና ስርጭት ላይ ተደረሰ። በአሁኑ ወቅት ሳይንቲስቶች በዚህ መላምት ላይ እርግጠኛ ለመሆን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። ቢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *