መፍትሄው ህጋዊ ከለላ ማበጀት ሳይሆን ድርድር ብቻ ነው አቶ ጃዋር መሀመድ
By: Date: April 30, 2020 Categories: ቃለ መጠይቅ

ኢትዮጵያ ለገጠማት ችግር የሽግግር መንግስት ከማቋቋም ጀምሮ ሌሎች ከፖለቲካዊ መፍትሔዎች ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት ጃዋር መሃመድ ተናገሩ። ብዙ ውዝግብ አዝሎ ለወራት ሲንከራተት የነበረው ሀገር አቀፍ ምርጫ ባልታሰበው ኮሮና ቫይረስ መክንያት ዝግጅዝግጅቱ ተገቷል፡፡

ትላንት የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተርር አብይ አሰተዳደርም ከዚህ ምርጫ ጋር ተያይዞ ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና እና የህግ አማራጮች በሚል ርዕስ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይት አካሄዶ ነበር።

ኢትዮጵያ በክረምቱ ማብቂያ ላይ ምርጫ ለማድረግ ብታስብም ጉዳዩ አስቸጋሪ በመሆኑ የግድ አማራጭ ሀሳቦች ተነስተው መስማማት ግድ በመሆኑ ነው መድረኩ የቀረበው ተብሏል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምክትል አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንዳሉት ችግሩን ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በማያፋልስ መልኩ ለመፍታት አራት የመፍትሄ አማራጮችን አስቀምጠዋል።

የመጀመሪያው አማራጭም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን ሁለተኛው ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ነው። ሶስተኛው ህገ መንግስት ማሻሻል ይህም የማይሆን ከሆነ ደግሞ የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ ናቸው ፡፡ ይህ ከተሰማ በኃላ በጉዳዩ ዙሪያ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከጃዋር መሀመድ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ አራቱም አማራጮች አያዋጡም ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባል የሆኑት አቶ ጃዋር መሀመድ እንደተናገሩት አራቱም አማራጮች ህጋዊ መሰረት የላቸውም። መፍትሄው ህጋዊ ሳይሆን ፖሊቲካዊ ስምምነት መፍጠር ነው ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

ለመሆኑ ፖለቲካዊ ስምምነት ወይም ውሳኔ ማለት ምን ማለት ነው? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ ይህ ማለት አሁን ያለው ህገመንግስታዊ ቀውስ ህጋዊ መፍትሔ ማግኘት አይችልም ሊኖር የሚችለው በፖለቲካ ፓርዎች መካከል በሚደረግ ውይይት እና ድርድር መፍትሔ ማበጀት ነው ብለዋል፡፡

ይህ ማለት ደግሞ የሽግግር መንግስት ከመመስረት ጀምሮ የተለያዩ መዋቅሮችን ማበጀትም ሊሆን ይችላል ይላሉ፡፡ እነዚህ አራት አማራጮች ህገመንግስታዊ ከለላዎች የሏቸውም ያሉ አቶ ጃዋር አሳማኝም አይደሉም ሲሉ ያክላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተጨማሪ የመንግስት ቅቡልነትም እንደማያስቀጥሉም ይጠቅሳሉ፡፡ እናም በነዚህ አራቱም መንገድ ከመስከረም 30 በኃላ ይህ መንግስት ህጋዊ እንደማይሆን አብራርተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *