ኢትዮጵያዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ዓመቱ ምርጥ ፕሬስ ፎቶ አሸናፊ ሆነ
By: Date: April 28, 2020 Categories: ፎቶግራፍ Tags:

በኢትዮጵያ የአሶሼትድ ፕሬስ የፎቶ ባለሞያ የሆነው ኢትዮጵያዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አየነ እጩ ከሆነባቸው ሦስት ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ውስጥ በዋና ዜና ታሪክ ስብስብ አሸናፊ ሆነ።

የፎቶ ባለሞያው ያሸነፈበት ስራው ቢሾፍቱ አቅራቢያ በወደቀው ቦይንግ ሰባት ሰላሳ ሰባት ማክስ ስምንት አይሮፕላን አደጋ የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ባለማግኘታቸው አውሮፕላኑ የወደቀበት ቦታ ሄደው ፊታቸው ላይ አፈር እየበተኑ ሲያለቅሱ በሚያሳይ አሳዘኝ ፎቶ ነው።

ላለፉት ስምንት አመታት በፎቶ ጋዜጠኝነት ሙያ ያገለገለው ሙሉጌታ አየነ ለዘንድሮው የዓለም አቀፍ ሽልማት የዓመቱ ፎቶ የአመቱ የፎቶ ታሪክ እና የዋና ዜና ታሪክ ምድቦች ታጭቶ የነበረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በዋና ዜና ታሪክ ስብስብ ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል። አሸናፊ የሆነበት ፎቶ አለም አቀፉ የዜና ወኪል የሆነላቸው በመላው አለም የሚገኙ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሀን ተቇማት በፊት ገፆቻቸው ላይ ተጠቅመውታል። በወቅቱም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በከፍተኛ ቁጥር የተጋራ ፎቶ ነበረ። ሙሉጌታ ሽልማቱን በማግኘቱ የተሰማውን ለቪኦኤ ሲገልፅ

በማሸነፌ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ይሄ ድል የኔ ብቻ አይደለም። የመላው አፍሪካዊ ወጣት ፎቶ አንሺዎች በፎቶ ጋዜጠኝነት ላይ መስራት እንዳለባቸው ይሰማኛል። አፍሪካውያን የራሳችንን፣ አገራችን ላይ የሚፈጠረውን ነገር በራሳችን አለም ላይ ማሳየት ይኖርብናል። ወጣት የአፍሪካ ፎቶ አንሺዎችንም የሚያነሳሳ ነው ብዬ ነው የማስበው ብሏል።

ሙሉጌታ ያሸነፈበት የዛሬ አመት ቢሾፍቱ አቅራቢያ በወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አይሮፕላን አደጋ ለሞቱ ቤተሰቦቻቸው ፊታቸው ላይ አፈር እየበተኑ ሲያለቅሱ የሚያሳየው ፎቶ እጅግ ስሜቱን የነካው ፎቶ እንደሆነ ይናግራል። ሙሉውን መረጃ እዚህ ይመልከቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *