በድንገተኛ ፍተሻ በርካታ ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ የተገኙ በቁጥጥር ስር ዋሉ
By: Date: April 27, 2020 Categories: ሀገራዊ

አዲስ አበባ ውስጥ መንግሥት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጣለውን ክልከላ በመጣስ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ አገኘኋቸው ያላቸውን አንድ መቶ አስራ ስድስት ሰዎችን መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ቢቢሲ ስለተያዙት ሰዎች የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፈንታን የጠየቀ ሲሆን ግለሰቦቹ ለጤና አደገኛ በሆነ ሁኔታ በአንድ ቦታ ላይ ተሰብስበው መገኘታቸውን አረጋግጠዋል።

ፖሊስ እንዳለው በሁለት ቀናት ውስጥ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ሰሜን ማዘጋጃ በሚባለው አካባቢ ባደረገው አሰሳ በአንደኛው ቤት ሰማኒያ አንድ በሌላኛው ቤት ደግሞ ሰላሳ አምስት ሰዎች በአንድ ላይ ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ እንደያዛቸው ፖሊስ ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *