
በዚህ ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የለንደን ማራቶን ታዋቂ ሯጮችን ብቻ ሊያሳትፍ እንደሚችል የውድድሩ ኃላፊ ሂዩ ብራሸር ተናግረዋል። ኃላፊው ውድድሩ ሊካሄድባቸው የሚችሉ አስር አማራጮች መቅረባቸውን አሳውቀው ጊዜው የበለጠ ሊራዘም እንደሚችል ጠቁመዋል።
ውድድሩ ነገ ሚያዝያ አስራ ስምንት ነበር ሊካሄድ ዕቅድ ወጥቶለት የነበረው። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደ መስከረም ሀያ አራት ተዘዋውሯል። ባለፈው ዓመት በታካሄደው ሩጫ አርባ ሶስት ሺህ ተወዳዳሪዎች መሳተፋቸው አይዘነጋም። ያለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን ለእርዳታ የሚሆን ሰማኒያ ሚሊዮን ዶላር ተዋጥቶበታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።