በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሻለ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት?

በኒውዚላንድ ጀርመን ታይዋንና ኖርዌይ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው የተነጠቁ ሰዎች ቁጥር በጣም ዝቅተኛ ነው። እነዚህን አገራት የሚያመሳስላቸው ይህ ብቻ ሳይሆን መሪዎቻቸም ሴቶች መሆናቸው ነው።

እኚሁ ሴት መሪዎች በዚህ ዓለም አቀፍ የጤና ቀውስ ወቅት የቫይረሱን መዛመት እንዲሁም የሟቾችን ቁጥር መቆጣጠር በመቻላቸው በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ሙገሳን እያገኙ ይገኛሉ። በመገናኛ ብዙሀን ዘንድም ‘ምሳሌ መሆን የሚገባቸውም’ በሚል እየተሞካሹ ነው። በቅርቡ ፎርብስ ባወጣው አንድ ፅሁፍ የእውነተኛ መሪነት ተምሳሌት ብሏቸዋል።

ሴት መሪዎች በዚህ ቀውስ ወቅት እንዴት አድርገን የሰውን ልጅ ህይወት መታደግ እንደሚቻል ለዓለም እያስተማሩ ነው በማለት የፎርብስ ጽሁፍ አትቷል። አገራት እየወሰዷቸው ባሉ እርምጃዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠትና፣ የሰውን ልጅ ህይወት እየታደጉ ያሉ መሪዎች በሴት የሚመሩ አገራት ቢሆኑም፤ በዓለማችን ያሉ ሴት መሪዎች ሰባት በመቶ ብቻ ናቸው።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመታገል ሴት መሪዎች እንዴት ሊሳካላቸው ቻለ? የቀደመ ምላሽ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት መሆኑን ተከትሎ የአይስላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ካትሪን ጃኮብስዶቲር በፍጥነት ተግባራዊ ያደረጉት እርምጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሕዝባቸውን መመርመር ነው።

ሦስት መቶ ስድሳ ሺህ ብቻ የሕዝብ ቁጥር ባላት አገራቸው ውስጥ በሽታውን ችላ ያሉት ጉዳይ አልነበረም። እርምጃ መውሰድ የጀመሩት ጥር ወር መጨረሻ አካባቢ ነው። በአገሪቷ በቫይረሱ የተያዘ ሰው መኖሩ ከመረጋገጡ በፊት ሃያና ከዚያ በላይ ሰዎች ሆኖ መሰብሰብ ተከለከለ።  ሙሉውን እዚህ ያንብቡ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *