በመጨረሻም ከወደ ጣልያን መልካም ዜና መሰማት ጀመረ

ለሳምንታት ሙሉ ያለማቋረጥ በሬሳ ሳጥን ተሞልተው የከረሙት የጣሊያን ቤተክርስትያናት እና የመቃብር ስፍራዎች ለመጀመሪያ ግዜ ካለ ወረርሺኙ ሰለባ አስክሬን ከፈን ውጪ መታየት እና መዋል ጀምረዋል። በዚህም ጣልያን በመጨረሻም የኮረና ቫይረስን እየረታችው እንደሆነ ተስፋ ሰጭ ሆኖ ተቆጥሯል።

ጣልያን 181,228 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት እና 24 ሺህ 114 ዜጎቿ ደግሞ እንደ ቅጠል የረገፉባት እስፔንን በማስቀደም ከአውሮፓ ሁለተኛ ተጎጂ ስትሆን ከአለም ደግሞ ከፊት አውራሪዎ አሜሪካ እና ስፔን ቀጥላ ሶስተኛ የቸነፈሩ ሰለባ ሆና ትገኛለች። ዴይሊ ሜይል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *