የ68 ዓመቷ ናይጄሪያዊት አዛውንት መንታ ልጆች ተገላገሉ
By: Date: April 20, 2020 Categories: አፍሪካ

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዜና የመገናኛ ብዙሃንን ባጨናነቀበት በአሁኑ ወቅት ከወደ ናይጄሪያ የተሰማው ዜና ብዙዎችን እያነጋገረ ነው ሲል ቢቢሲ በድረ ገጹ ዘግቧል። ክስተቱ አዲስ ባይሆንም ብዙም የተለመደና የሚጠበቅ አይደለም።

አንዲት ወደ ሰባ ዓመት የተቃረቡ አዛውንት ለወራት አርግዘው ጨቅላ ህጻናትን ታቅፈዋል። በዚህም የናይጄሪያው የሌጎስ ግዛት ዩኒቨርሲቲ መማሪያ ሆስፒታል አንዲት የስድሳ ስምንት ዓመት እናትን መንታ ልጆች በሰላም እንዲገላገሉ ማድረጉን አስታቋል።

የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ የህክምና አማካሪዎች ቡድን ሊቀ መንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ዋሲኡ አዲዬሞ እንዳሉት የስድሳ ስምንት ዓመቷ እናት በተሳካ ሁኔታ መንታ ህፋናትን የወለዱት ትናንት እሁድ ነው።

አዛውንቷ እናት መንታ ልጆቻቸውን የወለዱት በሰላሳ ሰባተኛ ወራቸው በቀዶ ህክምና መሆኑንም ዩኒቨርስቲው ጨምሮ ገልጿል። ከተሳካው የቀዶ ህክምና ማዋለድ በኋላ አራሷ የስድሳ ስምንት ዓመቷ እናት እና ልጆች በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ተነግሯል።

መውለድ አይቻልም በሚባልበት የዕድሜ ክልል የሚገኙት እናት ቀደም ሲል ምንም ልጅ ያልነበራቸው ሲሆን ትናንት የተገላገሏቸው መንታ ህጻንት የመጀመሪያ ልጆቻቸው ናቸው ተብሏል። ይህንንም ፕሮፌሰር ዋሲኡ አዲዬሞ የእኚህ እናት እርግዝና በዕድሜያቸው የመጀመሪያቸው መሆኑን  የናይጄሪያ የዜና የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *