በኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ መንገድ ተዋውቋል ይህን መንገድ እንሞክረዋለን የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ኦማር
By: Date: April 20, 2020 Categories: ሁነቶች

መሰረቱን እንግሊዝ ሀገር ያደረገው ዩኒቨርሳል ቲቪ በሶማሌው ማህበረሰብ ሰፊ ተመልካች ያለው የመገናኛ ብዙሀን ነው።በርካታ ፕሮግራሞች ሲኖሩት ጋዜጠኛ አብዱልሃፊዝ መሀመድ የሚያዘጋጀው ቃለመጠየቅ በሞጋችነቱ እና ስሱ ጉዳይን አንስቶ በማፋጠጥ አቀራረቡ ዝናን ያተረፈ በርካታ ታዋቂ የፖለቲካ ተክለስብዕና ያላቸው እንግዶች የሚቀርቡበት ሀርድ ቶክ አይነት ሾው ነው።

ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ኦማር ከዚህ ሞጋች ጋዜጠኛ ፕሮግራም ላይ እንደሚቀርብ ከተነገረ ጀምሮ በርካቶች በጉጉት ጠብቀውታል። እንደተገመተው የሞቀ ዱላ ቀረሽ በስሜት የተሞላ እና ኋላም በመከባበር የተቋጨ ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸው የተነሱትን ሁሉ ጥያቄዎች አላቀርብም። ሆኖም አንኳር አንኳር ጉዳዮችን ለመሸፈን ጥረት አደርጋለሁ። ብታነቡት እንደምታተርፉበት ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም። ሙክታሮቪች

ጋዜጠኛው ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር ለቃለመጠየቅ ፍቃደኛ ስለሆኑ ከልብ አመሰግናለሁ። በርካቶች በተለይ በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በፕሮግራሜ ላይ ስጋብዛቸው እሺ አይሉኝም። እርስዎ ፍቃደኛ በመሆንዎ ለድፍረትዎና የራስመተማመንዎ ሳላመሰግን አላልፍም።

ወደ መጀመሪያ ጥያቄዬ ልግባ እና ክልሉን እርስዎ ከመምራቶ በፊት የነበረበትን አጠቃላይ ሁኔታ እስቲ ለተመልካቾቻችን ጠቅለል ያለ ምስል ይስጡልን።

ሙስጠፋ: በአላህ ስም እጅግ ሩህሩህ እጅግ አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ መልሴን። እኔም በዚህ በርካታ የተከበሩ ሰዎች ሲቀርቡበት በነበረው ዝግጅትህ ላይ እንደቀርብ ስለተጋበዝኩ አመሰግናለሁ። ፍቃደኛ የሆንኩትም በአንተ ሚዛናዊ እና ሞያዊ ስነምግባር አድናቆት ስላለኝ እና ዩኒቨርሳል ቲቪ የክልላችንን ጉዳይ በዋነኝነት ሲዘግብ ስለነበረ አሁን ያለውን የሽግግርና የለውጥ ሁኔታ ለህዝባችን መረጃ ለመስጠት የእናንተን ፕሮግራም ምርጫዬ ስላደረግኩ ነው።

ወደ ጥያቄህ ስመጣ ክልሉን እኔ ከመረከቤ በፊት የነበረበት ሁኔታ እጅግ ለመናገር በሚከብድ ደረጃ የሶማሌ ህዝብ የተዋረደበት እንደማህበረሰብ ቅስሙ የተሰበረበት የሰውልጅ መሆኑ የተካደበትና ከፍተኛ እንግልት የደረሰበት ከአውሬ ጋር የታሰረበት አካላዊና መንፈሳዊ ማሰቃየቶች የተፈፀመበት ያለፍርድ ሰዎች በአሳቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት ሴቶች የተደፈሩበት እንዲሁ በጅምላ ሰዎች በአንድ መቃብር እየተረሸኑየሚቀበሩበት ክልል ነበረ።

ይህም የአለም ሰብአዊ መብት ተማጋች ድርጅቶችን ሪፖርት የተቀረፁ ምስሎችን ጭምር በማየት ማረጋገጥ ማንም ሰው የሚችለው ነው። ክልሉን ስንረከብ እንደ መንግስታዊ ተቋም የሚሰሩ የመንግስት መስሪያቤቶች አጠቃላይ የሉም። መዋቅራቸው ፈርሶአል። አጠቃላይ የክልሉ ቢሮክራሲን ሊያቀላጥፉ የሚችሉ መንግስታዊ ድርጅቶች ወድመዋል። በጣም በሚያሳዝን ደረጃ የነበረ ክልልን እና መንፈሱ የተሰበረ ህዝብን ነው ስንመጣ ያገኘነው። እንዲሁ በቀላሉ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።

ጋዜጠኛ: እርግጥ ነው የገለፁት ሁሉ እውነት ስለመሆኑ፣ ክልሉን በቅርበት ስለምከታተል ልክ ነዎት። ለውጥ መጥትዎ፣ እርስዎ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ያሳኳቸው ቁልፍ ተግባራትን እባክዎ ሊዘረዝሩልኝ ይችላሉ?

ሙስጠፋ: በርካታ ተግባሮችን እና ስኬቶችን በተጨባጭ አስመዝግበናል። ዝርዝሩ ብዙ ነው። ምናልባት ኋላ በሚነሱ ጥያቄዎች ዘርዘር አድርጌ እመለስበታለሁ። በአጠቃላይ ግን ለማስቀመጥ: የክልሉ ህዝብን አጠቃላይ ክብር ነው ወደ ቀድሞ ቦታው፣ ወደ የተከበረ እና የሚገባው የነበረ ስፍራ የመለስነው።

የወጣቶች ምናብና መንፈስን ነው አድሰን በሀገራቸው ተስፋ እንዲኖራቸው የራስ መተማመን እንዲኖራቸው፣ ማለም እንዲችሉ የተገፈፉትን ሰብአዊ ክብር መልሰን ለሀገር ልማት እንዲተጉ ወደሚያስችል ቁመና ከፍ አድርገናል ሞራላቸውን።

የሶማሌን ህዝብ ክብር በኢትዮጵያ ከፍ እንዲል፣ ሀገራችን ሰላሟ የተጠበቀ እንዲሆን፣ የሶማሌ ህዝብ ሰላም ወዳድ ህዝብ መሆኑን የቀጠናውን ሰላም በማስከበረ ምሳሌ እንዲሆን አድርገናል። በርግጥም የሶማሌ ህዝብ ሀይማኖተኛ፣ ሰው አክባሪ፣ ሰላም ወዳድ፣ ሀገር ወዳድ እንደሆነ እንዲያረጋግጥ እድሉን አመቻችተንለት ለኢትዮጵያም፣ ለምስራቅ አፍሪካም መልካም እሴቱን አሳይተናል። ስርዓት ሲስተካከል ህዝብ የዘመናት የሰላም ጥማቱን በተግባር አሳይቷል። ይህ እኛ በሀላፊነት በቅንነት በሰራነው የተቀናጀ ስራ የመጣ ውጤት ነው።

የሴቶቻችንን ክብር አስጠብቀናል። ከሁሉ በላይ በነፃነት መኖርን፣ ያለፍራቻ ወጥቶ መግባትን በክልሉ አስፍነናል። እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ የተማሩ የክልሉ የተማሩ ሰዎች፣ በመማራቸው እና በማወቃቸው መከበር ሲገባቸው የሚሸማቀቁበትን ስርዓት ለውጠን እውቀታቸውን ለማህበረሰባቸው እንዲያውሉ አስችለናል። ወደ ህዝብ አገልግሎት ስንጠራቸውም በችሎታ እና በችሎታ ብቻ መስፈርት ባደረግነው መሰረት አካታች የሆነ የሲቪል ሰርቪስ ስራን ተግባራዊ አድርገናል።

ከፈቀድክልኝ ትንሽ የማክለው ደግሞ ከዚህ ቀደም በአብዲሌ የዘረፋ ቡድን የተዘረፉ መሬቶች እና ያለህግ የተዘረፉ ንብረቶችን አስመልሰናል ለህዝብ። የህዝቡን ንብረት መዝረፍ የሚባል ነገር ተወግዷል። በጥቅም ትስስር እና በሞኖፖሊ የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ይደረግ የነበረውን የኢኮኖሚ የበላይነት ለአንድ ወገን ማመቻቸትን አስቀርተናል።

በተለይም የሰራነው ቁልፍ ተግባር፣ የሶማሌን ህዝብ ጥያቄ ወደ መሀል ሀገር ወስደን ከሀገሩ ሀብት በፍትሃዊነት የሚገባውን እንዲጠይቅ ወክለነው የሚያኮራ ስራ ሰርተናል። የሶማሌ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄን ወደ መሀል ሀገሪቱ አጠቃላይ ፖለቲካ አምጥተን በመሞገት ከተፈጥሮ ሀብቱ የሚጠቀምበትን መንገድ በእስትራቴጂ እና በእውቀት ታግዘን በኩራት አቅርበናል። በዚህም የኢትዮጵያውያንን ክብር እና ፍቅር አረጋግጠናል። የሶማሌ ህዝብ የሚገባውን ክብር እንዲያገኝ፣ የፖለቲካው የዳር ተመልካች ሳይሆን የመሀል ተጫዋች እና በሚወሰኑ ውሳኔዎች ድምፅ ሆነነዋል።

በመሰረተ ልማት ደረጃም በርካታ ተግባሮች ጀምረናል። የተጠናቀቁ እና በጅምር ላይ ያሉ በርካታ ናቸው። የክልላችን ህዝብ ዋነኛ ችግር መንገድ እንደሆነ ግልፅ ነው። በህጋዊ መንገድ ስርአታቸውን ጠብቀው ሰባት ረጃጅም ደረጃ አንድ አስፋልት ተጀምረዋል። እንግዲህ እነዚህ ፕሮጄክቶች ሲጠናቀቁ የምንመሰገንበት እንደሚሆን አምናለሁ። አየህ፣ መሰረተ ልማት ጊዜን ይወስዳል። ፍሬው ለመታየት ጥቂት አመታት ሊወስድ ይችላል። ለፖለቲካ ትርፍ አያገለግልም። ለሀገር ለወገን የሚሰራ ነው።

ወደ ሰላሳ ከተሞች የሀያአራት ሰዓት መብራት አስገብተናል። የጤና ሴክተሩንም ለማሻሻል ከዚህ ቀደም ከፌዴራል የሚላክልንን ብቻ የምንጠብቀው አሁን 150 አምቡላንሶችን በራሳችን ወጪ ገዝተን ለራቅ ራቅ ላሉ ወረዳዎች አስረክበናል።

ወደ 450 ት/ቤቶችን አስሩ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርቤት፣ ሶስት ቴክኒክ ኮሌጅ ሰርተናል። ወረዳን ከወረዳ የሚያገናኝ መንገድ፣ የከተሞች የውስጥ መንገዶችን አሰርተናል። አዲስ ሆስፒሎች እና እየታደሱ ያሉ ሆስፒታሎች፣ የደንብ ባንኮች፣ የፓርላማ ህንፃ እና የዞነን አስተዳደሮችን ህንፃዎች በአመት ከስምንት ወር ቆይታችን ውስጥ እያሰራን ነው። እውነት ለመናገር በአስር የመጨረሻ ወራት ከፍተኛ ስራዎችን አከናውነናል። ፖለቲካውን ካረጋጋን በኋላ ሰላም ካሰፈንን በኋላ የሰራነው ብዙ ነው። ዝርዝሩ ብዙ ነው። ከሁሉ በላይ ለልማት አመቺ የሆነውን ሰላም በክልሉ እውን ማድረጋችን ትልቁ ስኬታችን ነው።

 

ጋዜጠኛ: በዘረዘሩልኝ ስኬቶች ላይ የማነሳቸው ጥያቄዎች አሉኝ። ከዚያ በፊት፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ያላችሁ ግኑኝነት እንዴት ነው?

ሙስጠፋ: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መልካም ግኑኝነት ነው ያለን። በሀገሪቱ ህገመንግስት በተቀመጠው የፌዴራል እና የክልል የአሰራር እና የግኑኝነት ስርዓትና ደንብ ነፃነታችን ተጠብቆልን ነው የምንሰራው። አሁን ደግሞ በአንድ ፓርቲ፣ ብልፅግና፣ ስር በፓርቲ ደረጃ ስለምንሰራ መልካም የሆነ ገንቢ የሆነ ግኑኝነት ነው ያለን።

ጋዜጠኛ: ካነሱት አይቀር ይህ የብልፅግና ፓርቲ ነገር፣ በርካቶች ጥያቄ ያነሱበታል። የሶማሌ ህዝብን መብት ያስጨፈልቃል እያሉ አስተያየት የሚሰጡ አሉ። ክብር ፕሬዝዳንት፣ ብልፅግና ስትባሉ፣ የተባለው ብልፅግና እውነትም ብልፅግና ስለመሆኑ በምን አረጋግጠው አመኑ? በፓርቲዎ ውስጥም ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ሽኩቻ እና እስር ተካሂዷል፣ ከምዕራብ ሶማሌ ህዝብ ፓርቲ ጋርም ግጭት ውስጥ ገብታቹሀል።

ሙስጠፋ: አንድ በአንድ ዘርዘር አድርጌ እንድመልስልህ ጥያቄዎችህን በቅደም ተከተል አስቀምጥልኝ።  ጋዜጠኛው:
እሺ ከብልፅግና ፓርቲ እንጀምር

ጋዜጠኛ:

ክቡር ፕሬዝዳንት የብልፅግና ፓርቲ የሶማሌ ህዝብ እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበትን መብት ይገፋል። የሶማሌ ህዝብ ማንነቱ እና ባህሉን በነፃነት እንዳያራምድ እንቅፋት ይሆናል ብለው ቅሬታቸውን የሚያሰሙ አካላት አሉ። ብልፅግና ፓርቲ የተባለው እውነትም እንደተባለው ብልፅግና ለሶማሌ ህዝብ እንደሚያመጣ በምን አረጋግጣችሁ ነው የተቀላቀላችሁት?

ሙስጠፋ:

ብልፅግና ፓርቲ በምን መልኩ፣ እንዴት የሶማሌን ህዝብ እራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንደሚገፋ፣ እንዴት የህዝቡን ዴሞክራሲያዊ መብት እንደሚነጥቅ ዘርዘር አድርገው ማስረዳት ያለባቸው ብልፅግናን የሚቃወሙት ሰዎች ናቸው። ይህን ማስረዳት ያለባቸው እነሱ ናቸው።

እንግዲህ ተነጠቀ የሚባለው አንድ ነገር ቀድሞ በእጅህ ያለ ነገር ሲሆን ነው። አነሰ ተቀነሰ የሚባለው ቀድሞ ሙሉ የነበረ ነገር ነው። ሊሄድብን ነው የሚባለው ቀድሞ የነበረ ነገር ነው።

የሶማሌ ህዝብ በ28 አመት ውስጥ በሀቀኛ ዴሞክራሲ እና ነፃነት እራሱን አስተዳድሮ አያውቅም። ዴሞክራሲያዊ መንግስት አልነበረውም። እውነተኛ ፌዴራሊዝም ኖሮን አያውቅም። በህወሃት ባለስልጣናት የበላይ አዛዥነት የነበረ የሞግዚት አስተዳደር ነው የነበረው። አጋር ተብሎ የተገፋ፣ ከመሀል ሀገር የፖለቲካ ውሳኔ ውጪ ሆኖ የበይ ተመልካች እንዲሆን የተደረገ ክልል ነው። ጄኔራሎች የሚያስተዳድሩት፣ ሁሉ እየመጣ የሚዘርፈው፣ የሚገድለው እና የሚያስረው ህዝብ ነበረ በክልሉ።

በርዕዮተአለም ሳይቀር በይፋ የአርብቶአደርነት የኑሮ ዘይቤ ለአብዮታዊ ዴሞክራሲ የማይመጥን ኋላ ቀር ስለሆነ የሶማሌ ህዝብን የሚወክል የፖለቲካ ድርጅት ወደ ኢህአዴግ ፓርቲዎች መቀላቀል አይችልም ነው በመለስ ዜናዊ የተባልነው። ይህን ውርደት ነው እራስን በራስ ማስተዳደር ነበረ የሚባለው? ይህ ነው ፌዴራሊዝም? ይህ ነው እኩልነት? ይህ ነው ዴሞክራሲ?

እኛ እንደምናምነው የሶማሌ ህዝብ የነበረው እና የሚወሰድበት መብት የለም። ያልነበረ ነገር አይቀማም። ሀቀኛ ሆኖ በፌዴራሊዝም መርህ ላይ የተመሰረተ አስተዳደር የሶማሌ ህዝብ አይቶ አያውቅም። ያላየው ስርዓት ደግሞ አይናፍቅም፣ ተቀማሁ ብሎም አያዝንም። አሁን በብልፅግና ፓርቲ መንገድ ትክክለኛውን የራስን በራስ ማስተዳደር ሀቀኛ ፌዴራሊዝም እየጀመርን ነው።

ጋዜጠኛው:

እንደ እርስዎ እምነት የሶማሌ ህዝብን መብት ብልፅግና ፓርቲ ያስከብራል ነው እያሉን ያለው?

ሙስጠፋ:

በእርግጠኝነት! አሁን በያዝነው መንገድ የሶማሌን ህዝብ ወደ መካከለኛ የሀገሪቱ ፖለቲካ አምጥተን መብቱን እናስከብራለን። በፍትሃዊነት የድርሻችንን እንጠይቃለን። ብልፅግናን የተቀላቀልነው ሶማሌ ሆነን ነው። ባህላችን፣ እምነታችንን፣ እሴታችንን ይዘን ነው ወደ ብልፅግና የገባነው።

ከዚህ ቀደም ወደ መሀል ፖለቲካ መግባት አለብን፣ ተገልለናል፣ ወደ ዳር ተገፍተናል እያልን ስናኮርፍ ነበረ። አሁን እድሉን ስናገኝ ወደ ኋላ ማለት የለብንም። በኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ መንገድ ተዋውቋል። ይህን መንገድ እንሞክረዋለን።

ተቃዋሚዎቻችን ግን ለምን ብልፅግና የህዝቡን መብት ይገፋል እንደሚሉ እነሱን መጠየቅ ነው። ስትጠይቃቸውም፣ ለህዝቡ የሚያስቀምጡለትን አማራጭንም አብረህ ጠይቃቸው። አማራጫቸው ትናንት ሲገላቸው፣ ሲያሳድዳቸው እና በፌክ ፌዴራሊዝም ሲያታልላቸው የነበረውን የህወሓት መንገድ አይነት እንደማይሆን እምነት አለኝ። ብልፅግና መብትን ይገፋል የሚሉት አንዳንዶቹ ከዚህ ቀደም መብትን በመግፈፍ የሚታወቁ እንደተነቃባቸው እንኳን አውቀው ትንሽም የማያፍሩት ናቸው።

ጋዜጠኛ:

እንግዲህ ይህን ጉዳይ ህዝቡ፣ እንዲሁም ብልፅግናን የሚቃወሙት ሰዎች ቅሬታቸው ከምን እንደሆነ ለእነሱ የምተወው ይሆናል።

ወደ ሌላ ጥያቄ ልለፍ።

በክልሉ ቅድም እርስዎም እንደጠቀሱት ከፍተኛ ወንጀሎች ተፈፅመዋል። ህዝቡ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። በዚህ በኩል የርስዎ አስተዳደር ዳግሞ የህዝቡ ጉዳት እና ጉዳት ባደረሱት አካላት መካከል እርቅና መግባባት እንዲኖር አስፈላጊ ነው። ለተፈፀሙት ወንጀሎች ፍትህ የሚፈልግ ህብረተሰብም አለ። እንዲሁም ይህ ግፍ ለደረሰባቸው ግለሰቦች ከጉዳታቸው እንዲያገግሙም ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ የተሳካላችሁ ጉዳይ ካለ እና እክል የገጠማችሁ ነገር ካለም እባክዎ ይንገሩን።

ሙስጠፋ:

አንተም እንደምታውቀው የደረሰው ግፍና መከራ በጣም ከሚታሰበው በላይ ሰፊ እና በተወሳሰበ ደረጃ የተተገበረ፣ በመንግስት ደረጃ በጣም በጥንቃቄ ታቅዶበት የተፈፀመ ወንጀል ነው።

ለረጅም ጊዜ የተካሄደም እንደሆነ መረሳት የለበትም። ሁሉንም ጉዳይ ከስርመሰረቱ አጥርቶ ለማወቅ እና መረጃ ለመሰብሰብ በዚህ በአጭር ጊዜ ሊያልቅ የሚችል አይደለም። ፍትህ የማስገኘቱ ስራ አሁንም እየተሰራ ያለ ነው። ማስረጃዎችን በዶክሜንት ደረጃ የማጥራት ስራ ጊዜ የሚፈልግ ነው። ምክንያቱም ፍትህን ከበቀል መለየት አለብን። በጥድፊያ የሚሰራ ነገር ስህተት ሊኖረው ይችላል።

በሌላ በኩል ግን የዚህ ግፍና ወንጀል ሰለባ የሆኑትን ለመደገፍ ጥረት አድርገናል። ማህበር መስርተው እንዲንቀሳቀሱ፣ በኢኮኖሚ በምንችለው ደረጃ ደግፈናል። የጤና መቃወስ የገጠማቸውን አሳክመናል። ሆኖም የደረሰው ጉዳት በጣም አሰቃቂ ስለነበረ እውነት ለመናገር ሁሉን ነገር ብናደርግ እንኳ ጠባሳውን ማሻር አንችልም። ከባድ ስቃይ ነው የተፈፀመባቸው።

በርካታ ነገሮችን ሞክረናል። ሆኖም አጥጋቢ እንዳልሆነ ግን አምናለሁ።

ጋዜጠኛ

መልካም። ይህን ግፍ ሲቃወም ለዚህም ሲታገሉ የነበሩ ድርጅቶች ነበሩ። ስርዓቱ በርካታ በደል አድርሶባቸው የነበረ ለህዝባቸው የታገሉ አሉ። ከነዚህም ውስጥ ነፃ አውጪ ግንባር የነበረውና የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጪ ግንባር በመባል የሚታወቀው ድርጅት እና በእርስዎ አስተዳደር መካከል አለመግባባት እንዳለ ይነገራል። የፀባችሁ መንስዔ ምንድነው?

ሙስጠፋ

በእኛ እና በምዕራብ ሶማሊ ነፃ አውጪ ግንባር በሚባል ድርጅት መካከል የተፈጠረ ችግር የለም። ምክንያቱም በዚህ ስም እኛ የምናውቀው ድርጅት የለም። ከሌለ ድርጅት ጋር ደግሞ ልንጋጭ አንችልም።

 

ጋዜጠኛ:

በሌላ መንገድ ላስቀምጠው ጥያቄዬን። ከአማፂ ግንባርነት ወደ ፖለቲካዊ ፓርቲነት የተሸጋገረ አካል ጋር ስምምነት አድርጋችሁ ወደ ሀገር ገብቷል። ስምምነታችሁ ምን ነበረ?

ሙስጠፋ:

ከማን ጋር ነው ስምምነት የፈጠርነው? አንተ ስሙን የጠቀስከው ድርጅት ጋር ስምምነት አልፈጠርንም። በዚህ ስም የተደራደርነው አካል የለም እያልኩህ ነው።

ጋዜጠኛው

ኤርትራ ላይ ተደራድራችሁ ስምምነት ፈፅማችሁ ወደ ሀገር የገባ ድርጅት እኮ አለ ክብር ፕሬዝዳንት

ሙስጠፋ:

አንተ በገልፅከው ስም የሚጠራ አካል አይደለማ! ከማን ጋር እንደተደራደርን በትክክለኛ ስሙ ጠርተህ ጠይቀኝ እመልሳለሁ።

ጋዜጠኛ

ከግንባሩ ጋር አልተደራደርንም; እያሉኝ ነው?

ሙስጠፋ:

የትኛው ግንባር?

ጋዜጠኛው

ONLF የሚባለው ግንባር

ሙስጠፋ:

ፊደሎቹ የሚወክሉትን ቃላት ዘርዝርልኝ እስቲ

ጋዜጠኛ:

ምኑን ነው የምዘረዝረው ገለፅኩት እኮ

ሙስጠፋ:

እኔ እኮ ለመጠየቅ የፈለኩት አንተን ይህ በምህፃረ ቃል ያቀረብክልኝ ድርጅት ስሙ ማን ይባላል? ሙሉ ስሙን ጥቀስልኝ እና መልሱን ልስጥህ።

ጋዜጠኛ

ክቡር ፕሬዝዳንት እያወራሁ ያለሁት በስፋት ስለሚታወቅ ግንባር ነው። በዚህ ጊዜዎን ማባከን አልፈልግም። ግንባሩ ስሙ ምንም ይባል ምን ከመንግስት ጋር ስምምነት ፈፅሞ ወደ ፖለቲካ የገባ ድርጅት አለ። እኔም እርሰዎም እናውቀዋለን። የተስማማችሁት በምን ላይ ነው። አሁንስ ምን ችግር ተከሰተ? እንደሚሰማው ስልጣኖን ሊወስድ እንደሚችል ሰግተው ያልፈፀሙትን ወንጀል ፈፅመዋል እያሉ በሀሰት እንደሚከሷቸው ይነገራል። ስለዚህ ጉዳይ ሊመልሱልኝ ይችላሉ?

ሙስጠፋ

አንተ በምህፃረ ቃል ብቻ የጠቀስከው ድርጅት ሙሉ ስሙን መጥቀስ ካልፈለክ እኔ ልንገርህ።

Ogaden National Libration Front በመባል የሚጠራ ድርጅት ነው። ጥያቄህን የድርጅቱን ስም ጠቅሰህ ነው መጠየቅ ያለብህ።

ጥያቄህን የጀመርከው የምዕራብ ሶማሊያ ነፃ አውጪ ግንባር ብለህ ነው። በዚህ ስም የሚታወቅ የፖለቲካ ድርጅት ደግሞ የለም። በሌለ ድርጅት ላይ ደግሞ አስተያየት መሰጥት የለብኝ።

ለማለት የፈለከው እንደመሰለኝ።

WSLF በመባል ይታወቅ የነበረ ድርጅት ነው። West Somalia Liberation Front ይባል የነበረው ድርጅት ህልውናው 1980s ያከተመ ድርጅት ነው። ስለዚህ ስለዚህ ድርጅት የታሪክ ሰዎችን መጠየቅ እንጂ እኔን ስምምነት ፈፅመሀል ብለህ መጠየቅ የለብህም። ይህን ዝግጅት በርካታ ሰው ያየዋል። እኔ እና አንተ ብናውቀውም ሌላውን ሊያደናግር ስለሚችል መጠንቀቅ አለብን።

ጋዜጠኛ

ተቀብዬኣለሁ

ሙስጠፋ:

የሶማሌ ህዝብ እያዳመጠን ያለ በመሆኑ እውነቱን አፍረጥርጠን መነጋገር አለብን። ምዕራብ ሶማሌ በሚል የሚታወቅ ድርጅት ሳይሆን ከኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ድርጅት ተብሎ ከሚታወቅ ድርጅት ጋር ተደራድረን በብዙ ነጥቦች ላይ ስምምነት ላይ ደርሰናል።

ይህ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ የሚለውን ስያሜያቸውን ወደ አጠቃላይ የክልሉ የሶማሌ ህዝብ ሊወክል በሚችል ስም በመተካት ለክልሉ ህዝብ ሁሉ ወካይ ስም በራሳቸው ምርጫ እንዲሰይሙ አጠቃላይ መግባባት ነበረን።

ዘርዘር ለማድረግ

በመጀመሪያ ደረጃ በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ ፓርቲ ሆነው እንዲታገሉ እና አሁን የተገኘውን እድል በሰላማዊ መንገድ እንዲጠቀሙበት

የታጣቂ ወታደሮቻቸው ጉዳይን የምንፈታበት እና በትጥቅ ትግል ላይ ከመኖራቸው አንፃር የእነሱን ጉዳይ ማኔጅ የሚደረግበት መንገድን

በእኛ እና በእነሱ መካከል የፖለቲካ ውድድር የሚካሄድ በመሆኑ ስለዚህ ጉዳይ የተግባባንበትን ነጥቦችም አሉ

እኛ ቃል የገባነውን አደርገናል። በሞቀ እና በደመቀ ሁኔታ ተቀበ ለናቸዋል። ለአቀባበሉ እና ለወታደሮቹ መቋቋሚያ ከ5 ሚሊየን ብር ያህል አውጥተን መልካም አቀባበል አሳይተናል። ይህ ሁሉም ህዝብ የሚያስታውሰው ነው።

እንግዲህ ወደ ፖለቲካው ውድድር ሀሰብን ወደ መሸጥ ነው የተገባው። በዚህም አንዱ የሌላውን ሀሳብ ፍሬ ያለው ነው ወይስ የለውም፣ ያስኬዳል ወይስ አያስኬድም ወደ የሚል ትችት መግባት ያው የፖለቲካው አንድ አካል ነው የሚሆነው። ይህ የሀሳብ ትግል ነው። ከተከፉም በዚህ ነው እንጂ በምንም ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም።

ጋዜጠኛ:

እርስዎ ድርጅቱ ወንጀለኛ እንደሆነ፣ ደም ሲያፈስ እንደነበረ አንስተው የተናገሩበት አጋጣሚ የለም?

ሙስጠፋ:

እንደዚያ ብዬ አላውቅም።

ጋዜጠኛ

ይህ ድርጅት የፖለቲካ ስልጣን ሊይዝ ነው ከእርስዎ ጋር የሚወዳደረው። ያለእስርና ወከባ እንዲወዳደር ፍቃደኛ ነዎት

ሙስጠፋ:

መፍቀድ ብቻ አይደለም extra mile ሄደን በፖለቲካ ነፃ ውድድር እስከፈቀደልን ድረስ ፍቃደኝነታችንን አሳይተናል። ለዚህም ሽማግሌዎች ምስክር ናቸው። ውድድሩንም የሀገር ሽማግሌዎች እንዲታዘቡት የሚያስችል አሰራር ሁሉ ለመዘርጋት ተስማምተናል። በውድድር ለማሸነፍ ነው እቅዳችን።

ጋዜጠኛ:

ቅድም ዴሞክራሲ፣ ነፃነት፣ የህግ የበላይነት እና ስለሰብዓዊ መብት ብዙ ነግረውኛል። ሆኖም በክልሉ አሁንም በፖለቲካ ሳቢያ የሚታሰሩ ሰዎች አሉ። እስቲ በቅርቡ የታሰሩ አካላት ለምን እንደታሰሩ ሊነግሩኝ ይችላሉ?

ሙስጠፋ:

በጥቅሉ አትጠይቀኝ። የታሰረ ሰው አለ የምትለው ማን ነው? በስም ጠቅሰህ የታሰረን ሰው ጥቀስልኝ

ጋዜጠኛ

በርካታ ልጠቅስ እችላለሁ። በቅርቡ በነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት የታሰረ የርስዎ የፕሮቶኮል ሀላፊ አለ። አብዱል ቃድር ይባላል።

እንዲሁ ሌሎችም አሉ። ክቡር ፕሬዝዳንት በቅርብ የነበረው የፖለቲካ ሁኔታ ምንድነው መነሻው? ብዙ ስኬት ነግረውኝ አሁን ግን ክልሉ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለህዝብ ሊገልፁ ይችላሉ?

ሙስጠፋ

እየውልህ የሆነው ነገር እንዲህ ነው ……

ጋዜጠኛ:

ክቡር ፕሬዝዳንት በክልሉ በቅርቡ የተፈጠሩ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ እስር ተካሂዷል። በክልሉ ስለተፈጠረው ጉዳይ ሊነግሩን ይችላሉ? በተለይ የእርስዎ የፕሮቶኮል ሀላፊ የነበሩት አቶ አብዱል ቃድርን አስረውታል? ምክንያቱ ምንድነው?

ሙስጠፋ:

እኔ በግል ፀብ አላስርኩትም። የታሰረው በህግ ጥሰት ምክንያት ነው። ሀገር ነው የምንመራው። ሀገር በህግ እያስተዳደርን ነው። ህግ ሲጣስ ህጉ እኛንም እንድናስር ያስገድደናል። ሆኖም …..

ጋዜጠኛ: (ንግግራቸው አቋርጦ)

ምን ጥፋት አገኛችሁበት? የትኛውን ህግ እንደጣሰ ይህን ፕሮግራም በቀጥታ እየተከታተሉ ላሉት የተከበሩ ተመልካቾቻችን ሊነግሩ ይችላሉ?

ሙስጠፋ:

አይ አልናገርም

ጋዜጠኛ:

ክቡር ፕሬዝዳንት ለምን አይነግሩንም?

ሙስጠፋ:

የማልናገረው ለተከሳሹ መብት ስል ነው። የተከሳሹን የህግ ጥሰት በአደባባይ እኔ መሪ ሆኜ ከተናገርኩ የፍትህ ስርዓቱ ላይ አላስፈላጊ ጫና እናም አድሎ እንዳያመጣ ስጋት አለኝ። ማንም ሰው በህግ ፊት ንፁህ እንደሆነ የህግ ግምት አለ። በህገመንግስት የተቀመጠ ነው። እዚህ ያጠፋውን ብዘረዝር እራሱን ለመከላከል ከፍተኛ ጫና ሊኖርበት ነው። ህግ እየጣስኩ ህግ አስከብራለሁ የማለት ሞራል አጣለሁ።

ስለዚህ የማልናገረው ለተከሳሹ መብት፣ ፍትህ እና ደህንነት ስል ነው።

ጋዜጠኛ:

ምንም ጥፋት ሳይኖርበት አስረውት ቢሆንስ

ሙስጠፋ:

በፍርድቤት ስራ ጣልቃ መግባት ስለሌለብኝ ነው የህግ ጥሰቱን የማልነግርህ። ጠቅለል አድርጌ የምነግርህ እኛ ህግ ጥሷል ብለን በህግ ጥሰት ጠይቀነዋል። ህግ መጣስ አለመጣሱን ማጣራት ያለበት ፍርድቤት ነው። ያሻውን ያህል ምርጥ ምርጥ ጠበቆችን አሰልፎ መሟገት መብት አለው። እኛም አቃቤ ህግ መድበን እንሟገታለን። አስፈላጊ መስሎ ከታየን የችሎቱን ሂደት ለህዝብ በቀጥታ ልናስተላልፍም እንችላለን። ጋዜጠኛም ፍርድቤት ገብቶ ሊመለከት፣ በነፃነት ሊዘግብ ይችላል።

ጋዜጠኛ:

ህግ ያልጣሰ ከሆነስ

ሙስጠፋ:

ህግማ ጥሷል አልኩህ እኮ

ጋዜጠኛ:

የቱን ህግ

ሙስጠፋ:

በቅርቡ የተከሰተው ፖለቲካዊ አለመረጋጋትን ተያይዞ አሁን እዚህ በገለፅኩልህ ምክንያት የማልዘረዝረውን የህግ ጥሰት ፈፅሟል ብለን እናምናለን። ፍርድቤት ደግሞ የራሱን ፍርድ ይሰጣል። የችሎቱን ሂደት ቤተሰቡም ሆነ ፍላጎት ያለው ሰው መታደም ይችላል። በእስርቤት በህግ ለተጠየቁ ሰዎች በህገመንግስቱ የተረጋገጡለት መብቶች እንዳይነኩበት እኔው እራሴ ነኝ ትዕዛዝ ያስተላለፍኩት። ትዕዛዜ ተግባራዊ ስለመሆኑም ተከታትዬ እያጣራሁ ነው። እንደ መሪ ማድረግ ያለብኝ ይህን ነው።

ጋዜጠኛ:

የተፈጠረው እና እሱ በግል ተሳትፎበታል ያሉት ጉዳይ ምንድነው?

ሙስጠፋ:

የፖለቲካ አለመረጋጋት አልያም የፖለቲካ ክራይስስ ልንለው እንችላለን

ጋዜጠኛ:

እንዴት ያለ የፖለቲካ ክራይስስ?

ሙስጠፋ: (ፈገግ እያለ)

የፖለቲካ ክራይሲስ ብዬ ብጠቅሰው ነው እኔ የምመርጠው

ጋዜጠኛ:

የፖለቲካ ክራይሲስ ሲባል እንግዲህ መንግስት ለመገልበጥ ማሴር ሊሆን ይችላል። የፓርላማውን ስራ በህገወጥ መልኩ ማደናቀፍ እና ለህገወጥ ተግባር መመሳጠር ሊሆን ይችላል፣ አማፂ ማደራጀት ሊሆን ይችላል፣ እነዚህን የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላል። ከጠቀስኩት አንዱን መቼም ፈፅሞ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ነው የምታምኑት። አይደለም እንዴ ክቡር ፕሬዝዳንት? እስቲ አሁን ከጠቀስኳቸው የትኛው ሊሆን ይችላል?

ሙስጠፋ:

አንተ የመገመት መብት አለህ። እኔ ግን የፖለቲካ አለመረጋጋት ወይም ፖለቲካል ክራይሲስ በሚለው አገላለፅ እፀናለሁ

ጋዜጠኛ:

በክልሉ የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ማለትዎ ነው?

ሙስጠፋ:

የፖለቲካ ክራይሲስ ለመፍጠር የታሰበ ሴራ ነው ብዬ የማስቀምጠው

ጋዜጠኛ:

የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አልነበረም እያሉኝ ነው?

ሙስጠፋ:

የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ነውጥ ለመፍጠር አይነት ተደርጎ የሚወሰድ ነው

ጋዜጠኛ:

ምንም ጥፋት ሳይኖርበት አስረውት ቢሆንስ

ሙስጠፋ:

በፍርድቤት ስራ ጣልቃ መግባት ስለሌለብኝ ነው የህግ ጥሰቱን የማልነግርህ። ጠቅለል አድርጌ የምነግርህ እኛ ህግ ጥሷል ብለን በህግ ጥሰት ጠይቀነዋል። ቀሪው የፍትህ ስርአታችን ስራ ነው። ፍትሀዊ እንዲሆን የሚቻለውን ብቻ ሰይሆን በህግ የተቀመጠውን መብቱን ሁሉ እናስጠብቀለን።

ጋዜጠኛ:

መልካም። ሌሎች የታሰሩም አሉ። እነ ማህዲ ሀሰን ገፍዲድ የሚባል ሰው። ከደር ኦላድ የሚባል ሰው። እነዚህስ ምን አድርገው ነው?

ኸረ ብዙ ነገር የማነሳልዎት አለ።

ለምሳሌ እርስዎ ያቀረቡትን የደም ባንክ ተጠናቅቋል እወጃ፣ የጤና ሚኒስትሩ አለመጠናቀቁን አስተውቀዋል፣ ተናብባችሁ አትሰሩ ማለት ነው? የጂግጂጋ ከተማ ለህይወት መሰረታዊ የሆነውን ውሃ የተነፈገች ከተማ ናት። ውሃ የለም።

የፀጥታ ዘርፍ ሀለፊውን ለምን በሌላ ተኩ? ብዙ ጥያቄ ማንሳት ይቸላል።

እንደውም እርስዎ አክቲቪስት እንጂ ሀገር መምራት አይችሉም ይበለሉ።

ክቡር ፕሬዝደንት እውነቱን ለሶማሌ ህዝብ እንዲያሰውቁ እጠይቆታለሁ። ይመልሱልኝ!

ሙስጠፋ: (አየር ስቦ አስወጣ። ፈገግ አለ። በማዘን ጭንቅለቱን ከወዘወዘ በኋላ)

ስማ ማነህ አብዲልአፊዝ፣ እንዲህ ተብሎ አይጠየቅም

(ሙስጠፌ፣ የተቆጣ ይመስላል ……)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *