በአሜሪካ ኮሎራዶ “እናንተ ስራ ስትገቡ እኛ የማንገባበት ምክኒያት የለም” የሚሉ ነዋሪዎችና የህክምና ባለሙያዎች ጎዳና ላይ ተፋጠዋል

ምንም አንኳ አሜሪካ በኮረና ቫይረስ በአስከፊ ሁኔታ እየተጠቃች ቢሆንም ዜጎች ቫይረሱን ለመከላከል ከቤት እንዳይወጡ የተሰጠውን ተእዛዝ በርካታ ግዛቶች በማፍረስ ላይ ናቸው።

በእርግጥ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም እንዲሁ እገዳው በፍጥነት ተነስቶ ዜጎች ወደ ስራ መመለስ አለባቸው በማለት በተደጋጋሚ በመጎትጎት ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ይህን ተከትሎም ዛሬ በኮሎራዶ እንቅስቃሴ እንዳይጀመር የሚሉ የህክምና ባለሙያዎች አስፋልት ዘግተው የቆሙ ቢሆንም ነዋሪዎች ግን በዚህም ሊመለሱ አልቻሉም። እናንተ ስራችሁን እየሰራችሁ እኛን ልትከለክሉን አትችሉም በማለት ነዋሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ኒው ዮርክ ፖስት ዘግቧል።

ነጻነታችንን እንፈልጋለን ምንም ገደብ እንዲጣልብን አንፈልግም። እንዲህ ያለውን ስርዓት ከፈለጋችሁ ቻይና መሄድ ትችላላችሁ በማለት የህክምና ባለሙያዎችን አንጓጠዋል ሲል ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *