አሜሪካ የዓለም ጤና ድርጅትን መደገፍ ካቆመች አፍሪካ ያሰጋታል

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት የሚያደርጉትን የገንዘብ ድጋፍ ካቋረጡ በአፍሪካ የሚካሄዱ ፖሊዮን የማጥፋት ዘመቻዎች፣ የፀረ ኤች አይ ቪ ና የወባ እንቅስቃሴዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዱ ተገለፀ።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ የበላይ ኃላፊ ማትሲዲሶ ሞዬቲ አሜሪካ የፕሬዝዳንትን ውሳኔ ዳግም እንድታጤነው ጠይቀዋል። የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን በኮንግረስ በኩል መጽደቅ አለበት።

አሜሪካ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ድጋፍ አድራጊ ስትሆን በአሁኑ ወቅት ለሁለት ዓመት 151 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታ ነበር።

ከዚህ ገንዘብ ውስጥ የዓለም ጤና ድርጅት 50 ሚሊየን ዶላሩን የተቀበለ ሲሆን ነገር ግን የትራምፕ ድጋፍ የማቋረጥ ውሳኔ በአህጉሪቱ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ይጎዳዋል ተብሏል።

ከሚጎዱት ፕሮግራሞች መካከል አንዱ በተለያዩ አገራት የሚካሄዱ የመከላከል ስራዎች ናቸው። በአፍሪካ አሁንም 12 አገራት የፖሊዮ ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን ፖሊዮን ከአፍሪካ ለማጥፋትም በአህጉር ደረጃ እየተሰራ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ ከሚያካሄደው ስራ መካከል ደካማ የሆነውን የጤና ስርዓት መሆኑ ይታወቃል። የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ 300 ሚሊየን ዶላር በጅቶ ነበር። በአፍሪካ በአሁኑ ሰዓት ወደ 18 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ቢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *