ከአህያና ከዜብራ የተወለደችው ውርንጭላ

ኬንያ ውስጥ ካለ ፓርክ ወጥታ ወደ መንደር የተቀላቀለች አንዲት የሜዳ አህያ ከአህያ ተዳቅላ የተወለደውን የዞንኪ ውርንጭላ እዩት ሲል ሲ ኤን ኤን ከሰሞኑ ዘግቧል።

ከአህያ እና ከሜዳ አህያ የሚወለዱ ውርንጭሎች ዞንኪ በሚል ይጠራሉ፡፡ የዞንኪ ውርንጭላዋ እግሯ ላይ በደምብ ያልደመቀ የሜዳ አህያ ዥንጉርጉር መስመር ያለባት ከመሆኑ በስተቀር በአባቷ ወጥታ የተቀረው ነገሯ ሁሉ የአህያ ነው ብሏል ዘገባው፡፡

የዱር እንስሳት ተንከባካቢው ድርጅት ባልደረቦች የሜዳ አህያዋን እና የዞንኪ ውርንጭላዋን ወደ ቹሉ ብሄራዊ ፓርክ አዛውረዋቸው እንደልብ ሳርና ውሃ የሚያድን እንስሳ በሌለበት እየፈነጩ ነው ተብሏል፡፡

የሜዳ አህያ እርግዝና አስራ ሁለት ወራት ያህል ነው የዞንኪ ውርንጭላዋ ልክ እንደ በቅሎ ስለሆነች ለአቅመ ዞንኪነት ስትደርስ ራሷን መተካት አትችልም ይላል ዘገባው፡፡ ሸገር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *