ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም “የግድያ ዛቻ ደርሶብኛል” ሲሉ ተናገሩ
By: Date: April 8, 2020 Categories: ዜና

ዶ/ር ቴድሮስ “የግድያ ዛቻ ደርሶብኛል፤ እኔ ግን ግድ አይሰጠኝም” ሲሉ የተቃጣባቸውን ጥቃት ጠንከር ባሉ ቃላቶች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አጣጥለዋል።

“ከሁለትና ከሦስት ወር በላይ ዘረኛ ጥቃቶች ተሰንዝረውብኛል። ጥቁር ተብያለሁ። እውነቱን ለመናገር እኔ በጥቁርነቴ እኮራለሁ። የሚባለው ነገርም ግድ አይሰጠኝም” ሲሉም አክለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት፤ የዓለም ጤና ድርጅትን “በዋነኛነት በአሜሪካ ቢደጎምም፤ በጣም ለቻይና የወገነ ድርጅት ነው” ያሉ ሲሆን፤ ለድርጅቱ ድጋፍ ማድረጌን ላቆም እችላለሁ ሲሉም አስፈራርተዋል። ቢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *