የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የ48 ሰዓት የኮሮና ቫይረስ መግለጫ

ከድሬዳዋ የተላከው የ6 ሰዎች ናሙና ሁሉም ውጤታቸው ከቫይረሱ ነፃ ሆኗል። ቀደም ሲል በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠው ሁለት ጋር የቀረበ ግንኙነት የነበራቸው 37 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ የገቡ ሲሆን

ተጨማሪ 7 ሰዎችም ከበሽታው ጋር ተቀራራቢ ምልክቶችን በማሳየታቸው ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል። በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት በለይቶ ማቆያ 44 ሰዎች ይገኛሉ። በለይቶ ማቆያ ህክምና የሚገኙ ሁሉም በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *