የኮሮናቫይረስ ህሙማንን ለሚረዱ የጤና ባለሙያዎች 645 መኖሪያ ቤቶች ተዘጋጁ!

ለኮሮናቫይረስ ህመምተኞች እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች የሚያርፉባቸው ከ645 በላይ የመኖሪያ ቤት መዘጋጀታቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት ይህንን ወረርሽኝ በመቆጣጠርና ምላሽ በመስጠት ሂደት ውስጥ ትኩረት የሚሰጠው የጤና ባሙያዎች ጉዳይ ነው።ይህም የጤና ባለሙያዎቹ ከየተኛውም የኅብረተሰብ ክፍል በተለየ ለበሽታው ተጋላጭና ህይወታቸውንም አደጋ ላይ ጥለው ስለሚሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *