በኦሮሚያ ትምህርት በቤት ውስጥ ሊሰጥ ነው
By: Date: April 8, 2020 Categories: ዜና Tags:

በኮሮና ቫይረስ ትምህርት ቤቶች ቢዘጉም ተማሪዎች ባሉበት ትምህርታቸውን የሚከታተሉበትን አማራጭ ማዘጋጀቱን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት በሚቀጥለው ሳምንት ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው የሚማሩበትን የተለያዩ አማራጮች ለመግበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በክልሉ በ16 ሺህ ትምህርት ቤቶች 10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች እና 200 ሺህ መምህራን ይገኛሉ። በዚህም ተማሪዎቹ በሬዲዮ፣ በፕላዝማ፣ በሳታላይት እና በክልሉ ትምህርት ቢሮ ገጽ ቴሌግራም ቻናል አማራጮች ማግኘት እንደሚችሉ ነው የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ያስታወቁት።

ቢሮው አማራጮችን ቢያዘጋጅም ወረርሽኙ ሲያልፍ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸው ስለማይቀር፣ መምህራኑ አማራጮቹን ተጠቅመው ከወዲሁ መመዘኛዎችን እንዲያጠናቅሩ አሳስበዋል። ኢትዮ ኦንላይን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *