የታማሚዎቹ ሁኔታ

5ስቱ ከዱባይ የመጡ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው የዘጠኝ ወር ህጻንና ወላጅ እናቱ ይገኙበታል። አንድ የ25 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ከታይላንድ መጥታ በለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች።

አንድ የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን የንክኪ ሁኔታውም በመጣራት ላይ ይገኛል ብለዋል። ወጣቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው። የመጨረሻዋ የ30 ዓመት ሴት ኤርትራዊት ስትሆን ከእንግሊዝ ለንደን መጥታ በአዲስ አበባ በለይቶ ማቆያ ክትትል እያደረገች የምትገኝ ናት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *