አፍሪካ አሁንም ወደፊትም የኮሮና ቫይረስ ክትባት መሞከሪያ ልትሆን አትችልም – የዓለም ጤና ድርጅት

አፍሪካ አሁንም ሆነ ወደፊትም የኮሮና ቫይረስ ክትባት መሞከሪያ ልትሆን እንደማትችል የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶር ቴድሮስ አድሃኖም አስታወቁ።

የፈረንሣይ ሀኪሞች የኮሮና ቫይረስ ክትባት አፍሪካ ውስጥ ሊሞከር ይገባል የሚል አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ ዶር ቴድሮስ መግለጫውን ዘረኝነት ሲሉም አውግዘውታል።

ዋና ዳይሬክተሩ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ከዶክተኖቹ አስተያየት ጋር ተያይዞ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ከ ከቅኝ ገዢነት አስተሳሰብ የመጣ ሲሉ መግለጫውን ኮንነውታል።

ዶክተር ቴድሮስ አያይዘውም አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት የመፈተሻ ቦታ መሆን አትችልም ነው ያሉት። ከዚያም ባለፈ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይህንን ከሳይንስ ሊቃውንት መስማት ያሳፍራል። መግለጫውንም በአጽንኦት እናወግዛለን ይህ በአፍሪካ ምድር እንደማይፈጸምም ዋስትና እንሰጣለን” ብለዋል።

ምንም እንኳን ከመካከላቸው አንዱ ይቅርታን ቢጠይቅም ፈረንሳውያን ዶክተሮቹ በቴሌቪዝን በተደረገ ክርክር የሰጡት መግለጫ አፍሪካውያንን አስቆጥቷል። ምንጭ ቢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *