የትግራይ ክልል ፀጥታ ቢሮ ሓላፊ አቶ ተኪኡ ምትኩ ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፣ ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ የክልሉ መንግሥት ወስኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የተለቀቁት ታራሚዎች አንድ ሦስተኛውን የማረሚያ ቤት ቆይታቸውን ያጠናቀቁ፣ መልካም ሥነ ምግባር ያሳዩ እና ለይቅርታው ብቁ በመሆናቸው የተለዩ እንደሆኑም ተናግረዋል።
ታራሚዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር እንዲቀላቀሉ ትራንስፖርት በልዩ ሁኔታ እንደተዘጋጀላቸውም ገልጸዋል። ምንጭ፡- ኢዜአ