ፋይፍ ጂ ኢንተርኔት ኮረና ቫይረስን እያሰራጨ ነው የሚለውን ዜና የሰሙ እንግሊዛውያን የድርጅቱን ንብረት አወደሙ
By: Date: April 6, 2020 Categories: ዜና

የሞባይል ስልክ አገልግሎትን ፈጣንና ዘመናዊ ያደርገዋል ተብሎ የታመነበት የአምስተኛው ትውልድ ፋይፍጂ ቴክኖሎጂ የኮሮናቫይረስን እያሰራጨ ነው በሚል በተናፈሰው ወሬ ምክንያት በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው።

በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች በስፋት ሲዘዋወሩ በነበሩ ቪዲዮዎች ላይ እንደታየው ብሪታኒያ ውስጥ በሚገኙት በርሚንግሐምና መርሲሳይድ ከተሞች ውስጥ የሞባይል ግንኙነት ማማዎች በእሳት ሲጋዩ ታይተዋል።

ይህንን ተከትሎ የሴራ ንድፈ ሐሳብን በመመርኮዝ ዘመናዊው የአምስተኛው ትውልድ ቴክኖሎጂ ለኮሮናቫይረስ መሰራጨት ምክንያት ሆኗል የሚለው ክስ በሳይንስ ባለሙያዎች ሐሰት ተብሎ ተወግዟል።

አዲሱ ቴክኖሎጂ በሽታውን እያስተላላፈ ነው የሚሉ መላምቶችን የያዙ መልዕክቶች ዕውቅና ባገኙና በመቶ ሺህዎች ተከታይ ባሏቸው የፌስቡክ፣ የዩቲዩብና የኢንስታግራም አካውቶች በኩል ሳይቀር በስፋት ሲሰራጩ ነበር።

ነገር ግን ሳይንቲስቶች ይህ በኮረና ቫይረስ እና በፋይፍ ጂ አገልግሎት መካከል አለ የተባለው ግንኙነት ፍጹም የማይረባ ከመሆኑ በተጨማሪ ከሥነ ፍጥረት እሳቤ አኳያም ሊሆን የማይችል ነው ሲሉ አጣጥለውታል። ቢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *