ጃፓን የ6 ወራትየአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ልታውጅ ነው

ጃፓን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ዛሬ ወይም እስከ ዕሮባ ባለው ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደምታውጅ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ግልፀዋል፡፡

መንግስት ኢኮኖሚው ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ዝግጅት እያደረግኩ ነው ብሏል፡፡ ከ 3 ሺህ 5 መቶ በላይ ሰዎች በጃፓን በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል፡፡ 85 ያህሉ ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡

አንድ ሺህ ያህሉ ተጠቂዎች በመዲናዋ ቶኪዮ የተገኙ ሲሆን የተጠቂዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው ተብሏል፡፡ ዮሚዩሪ የተባለው የሀገሪቱ ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ዛሬ የአስአኳይ ጊዜ አዋጁን ይገልፃሉ ያለ ሲሆን ኪዮዶ የተባለው ሌላኛው ሚዲያ ደግሞ ዕሮብ ይታወጃል ብሏል፡፡

አዋጁ የግዛቶቹን ገዢዎች ህዝቡን በቤቱ እንዲቀመጥ ንግዶች እንዲዘጉ የማድረግ ስልጣን ይሰጣቸዋል መባሉን ሮይተርስ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *