ታክሲዎች የመጫን አቅማቸውን በግማሽ እንዲቀንሱና ተሳፈሪዎች እጥፍ እንዲከፍሉ ተወሰነ

የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል በአዲስ አበባ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች የሰው መቀራረብን ለመቀነስ ከመጫን አቅማቸው ግማሽ ብቻ እንዲጭኑና ተሳፋሪዎችም እጥፍ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡

የአንበሳ እና ሸገር አውቶብሶች ደግሞ ያለምንም የዋጋ ጭማሪ ሰላሳ ሰው ብቻ እንዲጭኑ ተወስኗል፡፡ውሳኔው ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንና ከሰዓታት በኋላ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ዝርዝር መረጃዎች እንደሚሰጡ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *