በመዲናዋ ህገወጥ ይዞታዎችን እያፈረሰ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር ገለፀ

በአዲስ አበባ የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ወቅታዊ ሁኔታን ተገን በማድረግ የመሬት ወረራዎች እየታዩ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል። በተለይም በቅርብ ጊዜያት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የመሬት ወረራው ታይቷል ነው ያለው። የከተማ አስተዳደሩም ህገወጥ ይዞታዎችን እያፈረሰ ሲሆን በቀጣይም እርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አስተዳደሩ የገለፀው።

ወቅታዊ ሁኔታ ተገን በማድረግ የሚደረጉ የመሬት ወረራዎችን ከማፍረስ በተጨማሪ ፈፃሚዎችና ተባባሪዎችን በህግ የሚጠይቅ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን ብሏል። በተለይም በቅርብ ጊዜያት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የመሬት ወረራው ታይቷል ነው ያለው። የከተማ አስተዳደሩም ህገወጥ ይዞታዎችን እያፈረሰ ሲሆን በቀጣይም እርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አስተዳደሩ የገለፀው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *