ዘመናዊነት፣ ማህበራዊ ተራምዶት እና የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሐኒት እና ሕክምና በአሰፋ ባልቻ መፅሐፍ በፒዲ ኤፍ
By: Date: April 5, 2020 Categories: የጤና መረጃ

ይህ የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒትና ህክምና የምዕተ ዓመት ጉዞየተሰኘ መጽሐፍ የዶክተር አሰፋ ባልቻ የዶክቶራል ዲግሪ ማሟያ ጥናት ላይተመስርቶ የተሰራ ነው። ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ የአገራችን የህክምናእውቀት እና ጥበብን በቀላሉ እንድንረዳ የሚያግዝ መፅሃፍ ነው። መጽሐፉ በአስር ዋና ዋና ምዕራፎች የተሰደረ ሲሆን ባህላዊ ህክምናንእናተዛማጅ ርዕሠ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

ይህ የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒትና ህክምና የምዕተ-ዓመት ጉዞየተሰኘ መጽሐፍ የዶክተር አሰፋ ባልቻ የዶክቶራል ዲግሪ ማሟያ ጥናት ላይተመስርቶ የተሰራ ነው። ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ የአገራችን የህክምናእውቀት እና ጥበብን በቀላሉ እንድንረዳ የሚያግዝ መፅሃፍ ነው። መጽሐፉ በአስር ዋና ዋና ምዕራፎች የተሰደረ ሲሆን ባህላዊ ህክምናንእናተዛማጅ ርዕሠ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

በመቅድሙ ፀሀፊውየታሪክ ትምህርት በአገራችን የቱንም ያህል ቢሰፋ ለባህላዊ ህክምናው እውቀት ዘርፍ በቂ የጥናት ሽፋን ሳይሰጠው መቅረቱን በአፅንኦት ያወሳሉ።  የባህላዊ መድሃኒት ቀማሚና የህክምናው ባለቤት የሆኑት ጠበብት መሰረታቸው ሃይማኖታዊ እንዲሁም አገርበቀል ጥልቅ እውቀት መሆኑ ፈጽሞ አይካድም። ቢሆንም ይህ አገር በቀል ዕውቀት በታሪክ ተገቢውን ቦታ ሲሰጠው አይታይም።

ከእኛው ፍፁም በተቃራኒ አቅጣጫ የምዕራባውያን የምርምር እና ልሕቀት ማዕከላት የእኛውን ዕውቀት የብራና ጽሑፎች እና ጥበባት ወደ ራሳቸው ቋንቋ በመመለስ እና ከዘመኑ ጋር አዛምደው በማጥናት ቀላል የማይባል እውቀት እየቀሰሙበት ይገኛሉ።

ከእነዚህ የረጅም ዘመናት ባህላው አና ሃይማኖታዊ የህክምና ዕውቀት እና ጥበባት ዘርፎች አንዱ የዕፀመድሃኒት አገር በቀል ዕውቀት ነው። ይህ ዘርፍ በአሁኑ ትውልድ ተገቢው እውቅና አልተቸረውም። አልያም ለወጣቱ ትውልድ በአግባቡ ማስተላለፍ አልተቻለም።

የዘርፉ አዋቂዎችም ስለራሳቸው እንዳይናገሩ ዕኩይ እደ ሰብ ደጋሚ አባይ ጠንቋይ አስማተኛ መተተኛ ስርማሽ ቅጠል በጣሽ የሚሉ መፀልማን እየተሰጣቸው እንዲሸማቀቁ ሆኑ። ከማህበራው እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ተገለለሉ። አይደለም ዕውቀታቸውን ለማውረስ በአግባቡ እንደዜጋ የሚገባቸውን ክብር በማጣታቸው ዕውቀት እና ክህሎታቸው የጋን መብራትእንዲሆን ተገደደ።

ቢሆንም አንድም ከሃይማኖታዊ ተገዥነት ሌላም ከግለሰባዊ ፍቅር አልያም ከምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳው አንጻር በማየት ሞያው ፍፁም እንዳይጠፋ ከማድረግ አንጻር አሁንም በቁርጠኝነት የሚታገሉ እና ለዛሬ ያደረሱን አዋቂዎች መኖራቸው መዘንጋት የለብንም። ኡእዚህን መጽሀፍ ሙሉ ቅጂ በፒዲ ኤፍ ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጫኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *