ባሎቻችን ከሌላኛዋ ሚስቶቻቸው ተፋቱ ደስ ብሎናል- ሶማሊያውያን በኮረና ቫይረስ ምክኒያት ጫት በመታገዱ የቤተሰባቸው ህይወት መሻሻሉን ገለጹ
By: Date: April 5, 2020 Categories: አፍሪካ,ዜና Tags:

ኮረና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት ባሌ ሌላ ሚስት ነበረው። ትላለች ሶማሊያዊቷ ሙና ኑር። “ከኮረና ቫይረስ መምጣት ወዲህ ግን ባሌን እጅግ ወድጄዋለሁ። ምክኒያቱም ከዚያችኛው ሚስቱ ጋር ተፋቷል። ጫት ለብዙ አመታት ባሌን የነጠቀችኝ ባላንጣዬ ነበረች።” ስትል ጫት የተባለው ቅጠል ምን ያህል ኑሮዋን እንዳመሳቀለው ትገልጻለች።

የሶማሊያ መንግስት ቫይረሱን ለመከላከል ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል የጫት ምርት ከኬኒያና ኢትዮጵያ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ማገድ ነበር።

ይህን ተከትሎም በሶማሊያ በርካታ ቤተሰቦች ደስተኛና የመተሳሰብ ህይወት መምራት መጀመራቸውን በተለያዩ መንገዶች በመግለጽ ላይ ናቸው።

ኢስት አፍሪካን ዴይሊ እንደ ዘገበው ከሆነ ከኬኒያ ብቻ በቀን እስከ ሀምሳ ቶን ጫት ወደ ሶማሊያ የሚገባ ሲሆን ኬኒያ ራሷ የጫት ምርት ከኢትዮጵያ እንዳይገባ በማገዷ ሳቢያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከአምስት ሚሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ማትረፏን መግለጿ ይታወሳል።

አሁን ባለቤቴን በጣም እወደዋለሁ። ምክኒያቱም ከዚህ በፊት በባዶ ሆዱ ከቤት ወጥቶ ጫቱን ሲያመነዥግ ውሎ ባዶ እጁን ይመለስ ነበር። አሁን ግን ወደ ቤት ሲመለስ በእጁ ወተት አትክልትና ፍራፍሬዎችን ይዞ ነው የሚመጣው ስትል ሙና እጅግ ደስተኛ መሆኗን ተናግራለች።

ይሁንና የሀገሪቱ መንግስት ከኮረና ቫይረስ ወረርሺኝ ማገገም በኋላ በጫት ላይ የጣለውን እገዳ ያንሳው አያንሳው የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ሙና እና በሚሊየን የሚቆጠሩ ሶማሊያውያን ግን ይህን ደስታቸውን እያጣጣሙ መቀጠል እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *