በዚህ የሀይማኖት ልዩነት የለም በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለአንድ ወር የሚቆይ ልዩ የጸሎትና የንሰሃ መርሃ ግብር ታወጀ፡፡
By: Date: April 5, 2020 Categories: ሀይማኖት

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በመላ የሃገራችን ክፍል ተግባራዊ የሚሆን ወቅታዊውን የኮሮና ወረርሽኝን በማስመልከት ለመላው ምዕመናን ሃገራዊ የጸሎት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ከመጋቢት ሀያ ስምንት ቀን ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ በመላው የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በቤታቸው ሆነው በጸሎት የፈጣሪን ምህረት የሚለምኑበት ጊዜ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዚህም መሠረት በነገው ዕለት በሶስት የተመረጡ ቦታዎች የጸሎት መርሃ ግብሩ የማስጀመርያ ፕሮግራም ይከናወናል ተብሏል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ የኃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና ወጣቶች ተሳታፊ ይሆናሉም ነው የተባለው፡፡

ወሩን በሙሉ በተመረጡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚወጣው መርሃ ግብር መሠረት የሃይማኖት አባቶች የሚያደርጉት ልዩ የጸሎትና የትምህርት ፕሮግራም ለህዝቡ በቀጥታ የሚተላለፍ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *