ድሮግባና ኤቶ የኮሮና ክትባት መጀመሪያ በአፍሪካ ሊሞከር ይገባል ያሉትን ፈረንሳያዊ ዶክተሮችን ነፍሰ ገዳዮች ሲሉ አወገዙ

ሁለት የፈረንሳይ ዶክተሮች በቴሌቪዥን ላይ በነበረ ውይይት የኮሮናቫይረስ የሙከራ ክትባት መጀመሪያ በአፍሪካ ሊሞከር ይገባል ማለታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ውግዘትን እያስተናገዱ ሲሆን ታዋቂዎቹ አፍሪካውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ዲዲየር ድሮግባና ሳሙኤል ኤቶም የሰላ ትችታቸውን ሰንዝረዋል።

አፍሪካ መሞከሪያ ላብራቶሪ አይደለችም። አፍሪካውያንም የላብራቶሪ አይጦች አይደለንም በማለት ድሮግባ በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል። የቀድሞው የካሜሮን እግር ኳስ ተጫዋች ሳሙኤል ኤቶ በበኩሉ ዶክተሮቹን ነፍሰ ገዳይ ብሏቸዋል።

ከቀናት በፊት በፈረንሳዩ የቴሌቪዥን ጣቢያ የቀረቡት ዶክተር ጂን ፖል ሚራና ዶክተር ካሚል ሎችት ውይይትንም ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻቸው አጋርተውታል። ዶክተሮቹ እንዳሉት ኤድስ ጥናቱ የተደረገው በአብዛኛው አፍሪካ ውስጥ ከመሆኑ አንፃር ኮረና ቫይረስ ክትባትም ሙከራ በአህጉሪቱ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

ይህንን ሙከራ ማድረግ ያለብን አፍሪካ አይደለም የፊት ጭምብሎች በሌለበት ህክምና በላደገበትና መተንፈስ ቢያዳግት እንኳን ትንፋሽ መመለስ የሚያስችል መሳሪያ በሌለበት መሆን አይገባውም ልክ እንደ ኤድስ በአፍሪካውያን የወሲብ ንግድ ተዳዳሪዎች ጥናት እንደተሞከረባቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *