የምስራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ የንግድ እና ልማት ባንክ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ጉዳት ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ አስታወቀ
By: Date: April 3, 2020 Categories: አፍሪካ,ዜና

የምስራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ የንግድ እና ልማት ባንክ TDB ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ጉዳት ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ አስታወቀ።

መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው የንግድና ልማት ባንክ ዋና ሰራ አስፈጻሚ አድማሱ ይልማ ዛሬ በኬንያ የኢፌዲሪ አምባሳደር ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ኢትዮጵያ ኮሮናን መከላከል እንድትችል የህክምና ቁሳቁስ መግዛት የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ባንኩ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ስራ አስፈጻሚው እንዳሉት ባንኩ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የንግድና የፍይናንሰ እንደሚሰጥ ጠቅሰው ለመንግሥት እና የግል ባንኮች ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት አለው ብለዋል።

አምባሳደር መለስ ዓለም ባንኩ ለኢትዮጵያ ባሳየው ድጋፍ አመስግነዋል። በሌላ በኩል በናይሮቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው የኮሮና ቫይረስን የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ናቸው ።

ኢትዮጵያዊያኑ ተደጋግፈን ይህንን የችግር ጊዜ አንለፍ በሚል መሪ ሀሳብ በአገር ቤት የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል። የኤምባሲው ዲኘሎማቶች የኮሮና መከላከል ዘመቻውን ለመደገፍ የአንድ ወር ደሞዛቸውን አበርክተዋል። ምንጭ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *