በጎንደር ከተማ ማነኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከነገ ጀምሮ አይኖርም

ከሌሎች አካባቢዎች ወደ ከተማዋ የሚያስገቡና ከከተማዋ የሚስወጡ የህዝብ ተከርካሪዎች መውጫና መግቢያ በሮቿን ደግሞ ከትናንት ጀምሮ ዘግታለች፡፡

የተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የኮሮና ተሐዋሲን ለመከላከል የተለያዩ ርምጃዎችን እየወሰዱ ነው፡፡ የጎንደር ከተማ አስተዳደርም ከትናንት ጀምሮ የተለያዩ ርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሸመ አግማስ ዛሬ ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደተናገሩት ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ርምጃ በከተማ ውስጥ በሚገኙ መዝናኛ ቦታዎችና የከተማ ውስጥ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ወሴኔ ተላልፏል፡፡

ምክትል ከንቲባው እንዳሉት መዝናኛ ስፍራዎች አዝማሪ ቤቶች መሸታ ቤቶች ጫት ቤቶችና ሌሎች ሰዎች በርከት ብለው የሚገለገሉባቸው ቦታዎች ከነገ ጀምሮ ለ14 ተከታታይ ቀናት አገልግሎት አይሰጡም፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በከተማው ውስጥ ጋሪዎችንና ሞተር ብስክሌቶችን ጨምሮ ማነኛውም የህዘብ አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪ በእገዳው እንደተካተተ ምክትል ከንቲባው አቶ ተሸመ አብራርተዋል፡፡

ምግብ ቤቶች ወንበራቸውን በግማሸቀንሰው አንዲያስተናግዱ ወፍጮ ቤቶችና ክሊኒክና ፋርማሲዎች ሳይዘጉ በጥንቃቄ ህቡን የሚያገለግሉ እንደሚሆኑም ምከትል ከንቲባው አመልክተዋል፡፡

አቶ ተሸመ አያይዘውም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ ከተማዋ የሚገባንና ከከተማዋ የሚወጣን የህዝብ ትራንስፖርት ማገዱንና ተግባራዊ መደረጉን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *