በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተደነገገውን የትራንስፖርት እገዳ የጣሰው አሽከርካሪ የሞት አደጋ አደረሰ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተደነገገውን የትራንስፖርት እገዳ የጣሰው አሽከርካሪ የሞት አደጋ አደረሰ። በድሬዳዋ አስተዳደር ሀርላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በአስተዳደሩ የተላለፈውን የህዝብ ትራንስፖርት እገዳ የጣሰው አሽከርካሪ የሞት አደጋ አድርሷል፡፡

ዛሬ ረፋድ ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ሚንባስ ተሸከርካሪ ከሀረር ወደ ድሬዳዋ አቅጣጫ ይጓዝ ከነበረአይሱዙ ጋር ተጋጭቷል፡፡ ግጭቱ ባደረሰው አደጋ በሚኒባስ ዉስጥ ተሳፍሮ የነበረ አንድ ታዳጊ ወጣት ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡

እገዳውን ተላልፎ ሲያሽከረክር የነበረው አሽከርካሪ የአካል ጉዳት ደርሶበት የህክምና እርዳታ እየተደረገለት እንደሚገኝም ተገልጿል:: አሽከርካሪው ከአደጋው ቀደም ብሎ በፖሊስ አባላት ማሽከርከርከሩን እንዲያቆምና የጫናቸውን ተሳፋሪዎች እንዲያወርድ ቢጠየቅም ጥሶ በመሄድ ከተወሰነ ጉዙ በኋላም በድጋሚ ሌሎች የፖሊስ አባላትን ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር አደጋው መድረሱን ከድሬደዋ ፖሊስ መረጃውን አግኝተናል፡፡ ዜናው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *