በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በተከሰተ ግጭት የሰው ሕይወት ጠፋ

በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በተከሰተ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ የግጭቱ መንስኤ ትናንት አንድ ግለሰብ ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን

ተከትሎ በግልገል በለስ ከተማ ከሌላ አካባቢ መጡ በተባሉ ወጣቶች መቀስቀሱን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል አንድ የከተማዋ ነዋሪ ዛሬ ሕይወት ማለፉንም ጠቁመዋል፡፡

ከሶስት እስከ አራት ሰዓት ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እንደነበረም ነዋሪቹ አመልክተዋል፡፡ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የግልገል በለስ ከተማ ዜሮ ሁለት ቀበሌ ነዋሪ ቀስት የያዙ ወጣቶች ወደ ከተማው በመግባት በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌላው የከተማይቱ ነዋሪው እንሚሉትም ትናንት በግልገል በለስ አካባቢ ሰላሳ የሚደርሱ ከብቶች ተሰርቀው የነበረ ሲሆን ከብቶቹን ለመመለስም ነዋሪዎች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን አስራ አራት የሚሆኑትን መመለስ መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት ደግሞ የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አቶ ሸሞ የተባሉ ግለሰብ መገደላቸውን ጠቁመዋል ክልል ልዩ ኃይል እና መከላከያ ሲተኩስ መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡ የመተከል ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፐክተር ጌታቸው ጅሬኛ በበኩላቸው በከተማው ዛሬ ጠዋት በተፈጠረው ግጭት አለመረጋጋት እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የሰው ሕይወት ማለፉንም ያረጋገጡ ሲሆን ዛሬ በነበረው ግጭት አንድ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ ላይም ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል፡፡ የከተማ ፖሊስ ጣቢያ ጭምር በድንጋይ መደብደቡን እና አንድ የፖሊስ መኪናም በወጣቶች በተወረወሩ ድንጋይ መሰባበሩን አክለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *