የ13 አመት ታዳጊን ጨምሮ ኤርትራ ሶስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
By: Date: April 1, 2020 Categories: አፍሪካ

የ13 አመት ታዳጊን ጨምሮ ኤርትራ ሶስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኤርትራ መንግሥት በረራ ከመከልከሉ በፊት ወደ አስመራ የተጓዙ የ32 አመት ወንድ እና የ52 አመት እንስት ዛሬ በኮሮና መያዛቸው መረጋገጡ ተገልጿል።

የ13 አመቷ ታዳጊ ቫይረሱ ከውጭ አገር ወደ አስመራ ከተጓዙ እናቷ እንደ ተላለፈባት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር መግለጫ ይጠቁማል። በአጠቃላይ በኤርትራ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 18 ከፍ ብሏል።

ከሕሙማኑ ሁለቱ የ32 ዓመት ወንድ እና የ52 ዓመት ሴት ሀገሪቱ በመንገደኛ በረራዎች ላይ እግድ ከመጣሏ በፊት ከባህር ማዶ ወደ ኤርትራ እንደገቡ ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ሦስተኛዋ ታማሚ የ13 ዓመት ልጃገረድ ስትሆን ከውጭ ሀገር ከመጣች እናቷ ቫይረሱ የተላለፈባት መሆኗን መግለጫው ጠቅሷል። እናትየውና የቤተሰቧ አባላት ባለፈው ሳምንት በለይቶ ማቆያ ተወሽበው እንደቆዩ የሚኒስቴሩ መግለጫ ተናግሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *