ጠልሰም ምንድነው?
By: Date: March 28, 2020 Categories: ታሪክ

ጠልሰም የተለየ ኀይል ያለው ጥበብ ነው። ኢትዮጵያውያን ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ይሰሩት የነበረ ጥበብ መሆኑም ይነገራል። ጠልሰም ምሥጢራዊ ጥበብ በጽሕፈትና በሥዕል ጥቅሎች የሚገለጽ እንደሆነ ይወሳል፡፡ በ‹‹መዝገበ ቃላት ሐዲስ›› አገላለጽ፣ ክታብና ሥዕል፣ ሐረግና ሰንጠረዥ፣ እንዲሁም ሙጭርጭር ጽሕፈት ነው፡፡

ይህም ጥበብ በየገዳማቱ በብራናዎች ላይ አርፏል። የጠልሰም ጥበብ ኃይል ያላቸውን ቃላት፣ዕፅዋት እንዲሁም ምልክቶችን ይይዛል።

ጠልሰም የመፈወስ ኃይል አለው ስለሚባል በክታብነት የሚጠቀሙበት አሉ። ይህ ጥበብ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ብቻ ተወስኗል።

የጠልሰም ስዕልም እነዚህን ኃይል ያላቸውን ቃላቶች፣ ምልክቶችና ዕፅዋት በመጠቀም የሚሳል ነው። ጠልሰም ከመፈወስ በተጨማሪ ሰውን የመሰወር፤ ግርማ ሞገስን መስጠት፤ በሰዎች ጫንቃ ላይ ለመስፈር የሚዳዳውን ሰይጣን ጋሻና ጦር በመሆን መከላከልና ማስጣል የሚያስችል ኃይል አለው ተብሎ ይታመናል፤ ይህም ዓቃቤ ርዕስ ተብሎ ይጠራል።

በኦርቶዶክሳዊ ምሰላና ተምሳሌትነት የቀረቡት ኪነ ቅቦች በቤተ ክርስቲያን ከሚታዩትና በሃይማኖታዊ መዛግብት ከሠፈሩት እንደ መስቀሎች፣ መላዕክት፣ የዳዊት ኮከብና የተለያዩ እንስሳት ያሉት ይታዩባቸዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *