የስብከት ጉባኤዎችና መንፈሳዊ ጉዞዎች እንዲቆሙ፣ በቅዳሴና በምሕላ ጸሎት ጊዜ ምዕመናን ተራርቀው እንዲቆሙ ታዘዋል
By: Date: March 21, 2020 Categories: ሀይማኖት,የጤና መረጃ,ጤና Tags:
ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የኮሮናቫይረስ በሽታን ለመከላከል ውሳኔ አሳለፈች
ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል የስብከት ጉባኤዎችና መንፈሳዊ ጉዞዎች ለጥቂት ቀናት እንዲቆሙ፣ በቅዳሴና በምሕላ ጸሎት ጊዜ በቤተ ክርስቲያንና በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምዕመናን ተራርቀው እንዲቆሙ ታዘዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያስችላል በማለት የደረሰበትን ውሳኔ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በኩል አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት ቅዱስ ሲኖዶቹ ቤተ ክርስቲያኗ ጸሎትና ምሕላ አጠናክሮ ከማድረግ በተጨማሪ ጤነኞችን የመጠበቅ፣ ሕሙማን የመንከባከብና የማጽናናት ኃላፊነት አለባት በማለት መደረግ ያለባቸውን ነገሮች አስቀምጧል።

ከእነዚህም መካከል ከቤተክርስቲያኗ ቀኖና ጋር የማይቃረኑ በሽታውን የመከላከያ መንገዶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ያዘዘ ሲሆን፤ ከአነዚህም መካከል አለመጨባበጥ፣ እጅን በሚገባ መታጠብ፣ ሳይጠጋጉ ዘርዘር ብሎ መቆም፣ በሳልና በማስነጠስ ጊዜ መጠንቀቅና በርቀት ሰላምታ መለዋወጥን ምዕመናኑና አባቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ተመክረዋል።

በተጨማሪም የስብከት ጉባኤዎችና መንፈሳዊ ጉዞዎች ለጥቂት ቀናት እንዲቆሙ፣ በቅዳሴና በምሕላ ጸሎት ጊዜ በቤተ ክርስቲያንና በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምዕመናን ተራርቀው እንዲቆሙ ታዘዋል።

EOTC TV

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *