ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ በኦስሎ የኖቤል ሽልማት መድረክ ላይ ስለጦርነት አስከፊነት ከተናገሩት
By: Date: December 11, 2019 Categories: ሁነቶች Tags:

በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሞቱትን ጓዶቼን ዛሬም ድረስ አስታውሳቸዋለሁ ስለ ቤተሰቦቻቸውም በጣም አስባለሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ በኦስሎ የኖቤል ሽልማት መድረክ ላይ ስለጦርነት አስከፊነት ከተናገሩት።

ጦርነትን አይተው የማያውቁ ነገር ግን ጦርነትን የሚያሞግሱና ሮማንቲክ የሚያስመስሉ አሉ። ጭንቀቱን አላዩም ድካሙን አላዩም የሚያስከትለውን ውድመት ወይም የልብ መሰበር አላዩም እንዲሁም ከጦርነቱ በኋላ የሚፈጥረውን የባዶነት ስሜት አልተሰማቸውም።

ጦርነት ለተሳተፉ ሁሉ የሲኦል ዋና ምልክት ነው ስሜቱን አውቀዋለሁ ምክንያቱም እዚያ ቆይቼ ስለተመለስኩ በጦር ሜዳ ወንድም ወንድሙን ሲያርድ ወይም ሲገድል አይቻለሁ አዛውንት ወንዶች ሴቶች እና ልጆች ሞት በሚፈነጥቀው በጥይት እና በተኩስ ፍንዳታ ሲሸማቀቁ አይቻለሁ።

እኔ በጦርነት ውስጥ ተዋጊ ሰው ብቻ አይደለሁም በጦርነት ያለውን የጭካኔ ተግባር እና በሰዎች ላይ ምን ሊደረግ እንደሚችል ምስክር ነበር ጦርነት መራራ ለሆኑ ወንዶች የተሻሉ ሰዎች እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ልበ ደንዳና እና ጨካኝ ሰዎችም ያደርጋል።

ከሃያ ዓመት በፊት በባድሜ ድንበር ከተማ ከሚገኝ የኢትዮጵያ ሠራዊት ክፍል አባል ሁኜ አንድ የሬዲዮ ከዋኝ ነበርኩ። ከተማው በሁለቱ አገራት መካከል የተካሄደውን ጦርነት ጥሎት ያለፈውን ጠባሳ ማሳያ ነበር መረጃ በሬዲዮ ለመስጠት የቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ገብቼ መረጃ ሰጥቼ ተመልስኩ።

የሚወስደው ጥቂት ደቂቃዎችን ብቻ ነበር። ሆኖም ስመለስ አባላቱ በከባድ መሳሪያ ተደምስሰው ሳገኛቸው ደነገጥኩ በእዚያ የተረገመ ቀን የሞቱትን ጓዶቼ ዛሬም ድረስ አስታውሳቸዋለሁ ስለ ቤተሰቦቻቸውም በጣም አስባለሁ።

ኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተደረገው ጦርነት አንድ መቶ ሺህ ወታደሮች እና ሲቪሎች ህይወታቸውን አጥተዋልን ከጦርነቱ በኋላ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቤተሰቦች እንዲፈርስ አድርጓል እንዲሁም በሁለቱም ወገኖች ማኅበረሰብ እስከመጨረሻው ጠባሳ ጥሎ አልፏል።

በጦርነቱ መሰረተ ልማቶች በመፈራረሳቸው ጦርነቱ ካበቃ በኋላ የኢኮኖሚ ጫና ተፈጥሯል የጦርነቱ ውጤት በጅምላ መፈናቀልን መተዳደሪ ማጣትን ዜጎችን ከሀገር መወጣት እና የዜጎችን ማውገዝ አስከትሏል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *